የጉብኝት መረጃ
መሥሪያ ቤታችንን ለመጎብኘት አስቀድመህ ቀጠሮ ማስያዝ ይኖርብሃል? አዎ። መጨናነቅ እንዳይፈጠርና ሁሉም ጎብኚዎች ዘና ብለው እንዲጎበኙ ለማድረግ ሲባል የሚመጡት እንግዶች በሙሉ (በጉብኝት ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሰዎች ብዛት ምንም ያህል ቢሆን) አስቀድመው ቀጠሮ ማስያዛቸው አስፈላጊ ነው።
አስቀድሞ ቀጠሮ ያላስያዘ ሰው መጎብኘት ይችላል? አስቀድመህ ቀጠሮ ካላስያዝክ መሥሪያ ቤታችንን እንድትጎበኝ ዝግጅት ማድረግ አስቸጋሪ ይሆናል። ካለው ቦታ አንጻር በአንድ ቀን ውስጥ ማስተናገድ የምንችለው የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን ጎብኚዎች ብቻ ነው።
ለጉብኝቱ ስንት ሰዓት መድረስ ይኖርብሃል? መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከቀጠሮህ ከ30 ደቂቃ በላይ ቀድመህ ባትመጣ ጥሩ ነው።
የጉብኝት ቀጠሮ ማስያዝ የምትችለው እንዴት ነው? “የጉብኝት ቀጠሮ አስይዝ” የሚለውን ጠቅ አድርግ።
ያስያዝከውን የጉብኝት ቀጠሮ መቀየር ወይም መሰረዝ ትችላለህ? አዎ። “የጉብኝት ቀጠሮህን ተመልከት ወይም ቀይር” የሚለውን ጠቅ አድርግ።
ለጉብኝት በመረጥከው ቀን ክፍት ቦታ ባይኖርስ? ለውጥ መኖሩን ለማየት አዘውትረህ ድረ ገጹን ተመልከት። የጉብኝት ቀጠሮዎች ሲቀየሩ ወይም ሲሰረዙ ክፍት ቦታ ልታገኝ ትችላለህ።
የጉብኝት ቀጠሮ አስይዝ
የጉብኝት ቀጠሮህን ተመልከት ወይም ቀይር
የጉብኝት ብሮሹር አውርድ
አድራሻ እና የስልክ ቁጥር
Av. Concha y Toro 3456
PUENTE ALTO
CHILE
+56 2 2428 2600
አቅጣጫውን ለማግኘት