በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ለደብዳቤዎቿ አድናቆታቸውን ገልጸዋል

ለደብዳቤዎቿ አድናቆታቸውን ገልጸዋል

 ብሩክ በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር የይሖዋ ምሥክር ናት። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት፣ የምትሰብከው ደብዳቤ በመጻፍ ነበር። ብሩክ በየሳምንቱ ብዙ ደብዳቤዎችን ትጽፋለች። ሆኖም ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ተስፋ መቁረጥ ጀመረች። እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለደብዳቤዋ ምላሽ የሰጠው አንድ ሰው ብቻ ሲሆን እሱም የጻፈላት ድጋሚ እንዳትጽፍለት ለመንገር ነው። ብሩክ ጥረቷ ከንቱ እንደሆነ ተሰምቷት ነበር።

 ከጊዜ በኋላ ግን፣ ባንክ ውስጥ የምትሠራ ኪም የተባለች ሌላ የይሖዋ ምሥክር ከአንድ ደንበኛዋ ጋር ስላደረገችው ውይይት ለብሩክ ነገረቻት። ደንበኛዋ ከይሖዋ ምሥክሮች ስለተላከለት በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ለኪም አጫወታት። በኋላ ላይ ኪም ደንበኛዋ እየተናገረ የነበረው ብሩክ ስለጻፈችው ደብዳቤ እንደሆነ ተገነዘበች! በቀጣዩ ሳምንት ይህ ደንበኛ ድጋሚ ወደ ባንክ ቤቱ መጣ። ከኪም ጋር እያወራ ሳለ በጉባኤ ስብሰባዎቻችን ላይ መገኘት ይችል እንደሆነ ጠየቃት፤ በወቅቱ ስብሰባዎቻችን የሚደረጉት በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ነበር።

 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዴቪድ የተባለ ሌላ የይሖዋ ምሥክር አንድ የሥራ ባልደረባው እሷ የጻፈችው ደብዳቤ እንደደረሰው ለብሩክ ነገራት። የሥራ ባልደረባው ደብዳቤው በእጅ የተጻፈ መሆኑ በጣም አስደንቆታል። “ለሌሎች በግለሰብ ደረጃ እንዲህ ያለ አሳቢነት የሚያሳዩ ተጨማሪ ሰዎች ቢኖሩ እንዴት ጥሩ ነው” በማለት ተናግሯል። ዴቪድ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ለግለሰቡ ተጨማሪ ምሥክርነት የሰጠው ሲሆን ጽሑፎችንም ሊያመጣለት እንደሚችል ገለጸለት፤ ግለሰቡም ግብዣውን በደስታ ተቀበለ።

 የይሖዋ ምሥክሮች፣ በአገልግሎታቸው ላይ የዘሩት ዘር እንዴት እንደሚበቅል ላያውቁ እንደሚችሉ ይገነዘባሉ። (መክብብ 11:5, 6) ብሩክ ያገኘችው ይህ ተሞክሮ በአገልግሎት በምታበረክተው አስተዋጽኦ ደስተኛ እንድትሆን አድርጓታል።—1 ቆሮንቶስ 3:6