ስለ እኛ

የይሖዋ ምሥክሮች እነማን ናቸው?

እኛ የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ የምንገኝ ሃይማኖታዊ ቡድን ነን። የምናመልከው ይሖዋን ነው፤ ይሖዋ፣ ፈጣሪ እና ሁሉን ቻይ አምላክ ነው። (መዝሙር 83:18፤ ራእይ 4:11) ክርስቲያኖች ነን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክ ልጅ እና አዳኛችን እንደሆነ እናምናለን። (ዮሐንስ 3:16፤ የሐዋርያት ሥራ 4:10-12) የምናምንባቸው ነገሮች በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ስለ እምነታችን ይበልጥ ማወቅ ከፈለግህ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የምታገኘውን መረጃ ከራስህ መጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንድታመሣክር እንጋብዝሃለን።

ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማወቅ ትፈልጋለህ? የሚለው ቪዲዮ ስለ እኛ ተጨማሪ መረጃ ይሰጥሃል፤ ለምን አትመለከተውም?

አኃዛዊ መረጃዎች

የየአገሩ መረጃ

ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ?

ስለምናምንባቸው 15 መሠረታዊ ነገሮች ጠቅለል ያለ ግንዛቤ ለማግኘት አንብብ።

የይሖዋ ምሥክሮች አንዳንድ በዓላትን የማያከብሩት ለምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች በዓላትን ከማክበር ጋር በተያያዘ ውሳኔ ሲያደርጉ እነዚህን አራት ጥያቄዎች ያስቡባቸዋል፤ እስቲ እነዚህን ወሳኝ ጥያቄዎች ተመልከት።

የይሖዋ ምሥክሮች ልደት የማያከብሩት ለምንድን ነው?

ከልደት ጋር የተያያዙ አራት እውነታዎችንና አምላክ በእነዚህ የልደት በዓል ገጽታዎች የማይደሰተው ለምን እንደሆነ ተመልከት።

የይሖዋ ምሥክሮች ደም የማይወስዱት ለምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች ደም ስለመውሰድ ካላቸው አቋም ጋር በተያያዘ ብዙ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች አሉ። በዚህ ረገድ ያለን አቋም ምን እንደሆነ ሐቁን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያኖች ናቸው?

ክርስቲያን ተብለን የምንጠራው ለምን እንደሆነ እንዲሁም ክርስቲያን ተብለው ከሚጠሩ ሌሎች ሃይማኖቶች የምንለየው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ጥረት እንድታደርግ እናበረታታሃለን።

ሌሎች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ እኛ ልታነሳቸው ትችላለህ ብለን ላሰብናቸው በርካታ ጥያቄዎች የሰጠነውን መልስ ተመልከት።

ከእኛ ጋር ለመገናኘት

አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ትፈልጋለህ?

መልስ ያላገኘህለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ አለ? ወይም ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማወቅ ትፈልጋለህ? አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ጥያቄ አቅርብ።

በስብሰባዎቻችን ላይ እንድትገኝ ጋብዘንሃል

ስለ ስብሰባዎቻችን ማወቅ ትፈልጋለህ? ለአንተ ቅርብ የሆነው የመሰብሰቢያ ቦታ የት እንደሆነ እዚህ ገጽ ላይ መፈለግ ትችላለህ።

ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ለመገናኘት

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮዎች አድራሻ።

የቤቴል ጉብኝት

በአቅራቢያህ የሚገኝን ቅርንጫፍ ቢሮ የጉብኝት ፕሮግራም ተመልከት።