በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 15, 2019
ፖላንድ

ዋርሶ፣ ፖላንድ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ዋርሶ፣ ፖላንድ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከነሐሴ 9-11, 2019

  • ቦታ፦ በዋርሶ፣ ፖላንድ የሚገኙት የሌጊያ ዋርሶ ስታዲየም እና ቶርቫር ሆል

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ እንግሊዝኛ፣ ፖሊሽ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 32,069

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 190

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 6,892

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሃንጋሪ፣ ማዕከላዊ አውሮፓ፣ ሞልዶቫ፣ ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ኢኳዶር፣ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዩክሬን፣ ጃፓን፣ ጆርጂያ፣ ፈረንሳይ፣ ፊንላንድ

  • ተሞክሮ፦ የፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ዋርሶ ሞኮቶቭ (ልዑካኑ ካረፉባቸው ሆቴሎች መካከል አንዱ) ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ካሚል ካዝሜርኬቪዬች እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦ “ከእናንተ ጋር አብሮ መሥራት ቀላል ነው፤ ሁሉም ደንበኞቼ እንደ እናንተ ደግና አዎንታዊ ቢሆኑ ደስ ይለኝ ነበር። እንደምትዋደዱና አንድነት እንዳላችሁ በግልጽ ማየት ይቻላል። . . . ላከናወናችሁት በሚገባ የተደራጀ ሥራ አድናቆቴን መግለጽ እፈልጋለሁ።”

    አውቶቡስ ለማቅረብ የተቀጠረው ኬ ኤል ቲም የተባለ ድርጅት ባለቤት የሆኑት ካሚል ሉባንስኪ እንዲህ ብለዋል፦ “ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር አብረን መሥራት ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ከእነሱ ጋር መሥራት አስደሳች እንደሚሆን ገብቶኝ ነበር። በጣም የተደራጁ ናቸው። ይህ ሰፊ ዝግጅት በሚገባ የታሰበበትና በደንብ የታቀደ ነበር። የአገሪቱን መንግሥት ጨምሮ ድርጅታችን ታዋቂ የሆኑ በርካታ ደንበኞች አሉት፤ በአገራችን ውስጥም ሆነ በሌሎች የአውሮፓ አገራት በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ ተካፍለናል። ሆኖም የእናንተን ያህል የተደራጀ ደንበኛ ብዙም አላጋጠመንም። ሹፌሮቻችንና ሌሎች ሠራተኞቻችን ስለ ይሖዋ ምሥክሮች የሚናገሩት መልካም ነገር ብቻ ነው። ወደፊትም በድጋሚ አብረን እንደምንሠራ ተስፋ እናደርጋለን።”

 

ልዑካኑ በአውሮፕላን ማረፊያ ሞቅ ያለ አቀባበል ሲደረግላቸው

ተሰብሳቢዎች ዓርብ ጠዋት ወደ ስብሰባ ቦታው ሲገቡ

ስብሰባው ከተደረገባቸው ቦታዎች አንዱ ማለትም የሌጊያ ዋርሶ ስታዲየም ከላይ ሲታይ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጌሪት ሎሽ የዓርቡን የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ

ቅዳሜ ቀን ከተጠመቁት መካከል ሦስቱ

ወንድሞችና እህቶች ስብሰባውን በጥሞና ሲከታተሉ

የባሕል ልብስ የለበሱ ልዑካን ከስታዲየሙ ውጪ ፎቶግራፍ ሲነሱ

እሁድ ቀን፣ ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የመደምደሚያውን መዝሙር ከተሰብሳቢዎቹ ጋር ሲዘምሩ

ወጣት እህቶች ምሽት ላይ በተካሄደው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ ለተገኙት ልዑካን ሲዘምሩ

ወንድሞች እና እህቶች ምሽት ላይ በተካሄደው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ የፖላንድን ባሕላዊ ውዝዋዜ ሲያሳዩ