ታኅሣሥ 22, 2021
ፊሊፒንስ
ራይ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ ከባድ ውድመት አስከትሏል
ራይ (የአካባቢው ሰዎች ኦዴት ብለው ይጠሩታል) የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ከታኅሣሥ 16 እስከ 18, 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በፊሊፒንስ ያሉ የተለያዩ አካባቢዎችን መትቷል። አውሎ ነፋሱ መጀመሪያ የመታው የሻጋው ደሴትን ሲሆን በወቅቱ በሰዓት 195 ኪሎ ሜትር የደረሰ ከፍተኛ ፍጥነት ነበረው። በሰሜን ሚንዳናው፣ በደቡብ ሉዞን እና በቪሳያስ ያሉ አካባቢዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
የሚያሳዝነው 4 አስፋፊዎች ሞተዋል
1 አስፋፊ አሁንም የደረሰበት አልታወቀም
12 ወንድሞችና እህቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል
ከ2,000 የሚበልጡ አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
246 ቤቶች ፈርሰዋል
327 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
1,174 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
43 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የእርዳታ ሥራውን የሚያስተባብሩ 6 የአደጋ ጊዜ እርዳታ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል
የአካባቢው ሽማግሌዎች የሚወዷቸውን ሰዎች በሞት ያጡትን ጨምሮ በአደጋው የተጎዱ ወንድሞችንና እህቶችን እያጽናኑ ነው
የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው
አደጋው ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ያሉ ወንድሞችና እህቶች የሽማግሌዎችን አመራር በመከተል፣ በአውሎ ነፋሱ ለተጎዱ ወንድሞችና እህቶች ምግብና ልብስ ሰጥተዋል። የተለያዩ ምግቦች ከዳቫው ሲቲ፣ በሱሪጋው ሲቲ ወዳሉ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ወዲያውኑ ተከፋፍለዋል።
በዚህ አደጋ ምክንያት ውድ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በማጣታችን በጣም አዝነናል። በዚህ “ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን” ውስጥ ስንኖር መጽናኛና ብርታት ለማግኘት በይሖዋ መታመናችንን እንቀጥላለን።—2 ጢሞቴዎስ 3:1