መጋቢት 9, 2021
ጋና
የይሖዋ ምሥክሮች የተሻሻለውን አዲስ ዓለም ትርጉም በችዊ (አኩዋፔም) ቋንቋ አወጡ
መጋቢት 7, 2021 የይሖዋ ምሥክሮች የተሻሻለውን አዲስ ዓለም ትርጉም በችዊ (አኩዋፔም) ቋንቋ አወጡ። አስቀድሞ በተቀረጸ ንግግር አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን ያበሰረው የበላይ አካል የሆነው ወንድም ኬነዝ ኩክ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ የኤሌክትሮኒክ ቅጂ ከፕሮግራሙ በኋላ ወጥቷል።
ፕሮግራሙ በሳተላይት የቴሌቪዥን ጣቢያ አማካኝነት ተላልፏል። ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ አስፋፊዎች ደግሞ ፕሮግራሙን በስልክ መከታተል ይችሉ ነበር። በዚህ መንገድ 98,000 ከሚሆኑት ችዊ ተናጋሪ አስፋፊዎች አብዛኞቹ ፕሮግራሙን መከታተል ችለዋል።
ችዊ፣ ጋና ውስጥ በስፋት የሚነገር ቋንቋ ነው። ችዊ የተለያዩ ቀበልኛዎች ቢኖሩትም አኩዋፔም ችዊን አብዛኞቹ የችዊ ተናጋሪዎች ይረዱታል። መጽሐፍ ቅዱሱን የተረጎመው ስድስት ተርጓሚዎችን ያቀፈ ቡድን ሲሆን ሥራውን ለማጠናቀቅ ሦስት ዓመት ተኩል ወስዷል።
አንድ ተርጓሚ እንዲህ ብሏል፦ “ይህን በጣም አስፈላጊ ሥራ እንድናከናውን ኃይል የሰጠን ይሖዋ ነው። አምላክ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች ቃሉን እንዲያገኙ እንደሚፈልግ ይበልጥ እርግጠኛ ሆኛለሁ።”
ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በመውጣቱ ከችዊ ተናጋሪ ወንድሞቻችን ጋር እንደሰታለን። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የአምላክ ቃል ኃይልና ጥበብ እንደሚሰጠን እንተማመናለን።—መዝሙር 19:7