በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጆርጂያ

ታሪካዊ እመርታዎች በጆርጂያ

ታሪካዊ እመርታዎች በጆርጂያ
  1. ጥር 17, 2017—የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት በትሳርሲጅ ስም ከተከፈተው ክስ ጋር በተያያዘ ያስተላለፈው ብይን፣ የጆርጂያ ዳኞችና ሕግ አስከባሪ አካላት የይሖዋ ምሥክሮችን በሃይማኖታዊ ጥላቻ ተነሳስተው የኃይል ጥቃት ከሚፈጽሙባቸው ሰዎች መጠበቅ እንዳልቻሉ አሳየ

    ተጨማሪ መረጃ

  2. ታኅሣሥ 10, 2014—የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያናዊ ጉባኤ በጆርጂያ ሕጋዊ እውቅና አገኘ፤ ይህም የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ማኅበር በአገሪቱ የተሻለ ቦታ እንዲሰጠው አድርጓል

  3. ጥቅምት 7, 2014—የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት በቤግሄሉሪ ስም ከተከፈተው ክስ ጋር በተያያዘ ያስተላለፈው ብይን፣ የጆርጂያ ሕግ አስከባሪ አካላት የይሖዋ ምሥክሮችን በሃይማኖታዊ ጥላቻ ተነሳስተው የኃይል ጥቃት ከሚፈጽሙባቸው ሰዎች መጠበቅ እንዳልቻሉ አሳየ

    ተጨማሪ መረጃ

  4. ሚያዝያ 6, 2013—የይሖዋ ምሥክሮች በተብሊሲ ያለውን ቢሯቸውን አስፋፉ

  5. ግንቦት 3, 2007—የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት በግልዳኒ ስም ከተከፈተው ክስ ጋር በተያያዘ ያስተላለፈው ብይን፣ የጆርጂያ ሕግ አስከባሪ አካላት የይሖዋ ምሥክሮችን በሃይማኖታዊ ጥላቻ ተነሳስተው የኃይል ጥቃት ከሚፈጽሙባቸው ሰዎች መጠበቅ እንዳልቻሉ አሳየ

  6. ኅዳር 28, 2003—በዩናይትድ ስቴትስ ያለው የዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ ኦቭ ፔንስልቬንያ ቅርንጫፍ በጆርጂያ ድጋሚ እውቅና አግኝቶ ተመዘገበ፤ ብዙም ሳይቆይ በወንድሞች ላይ የሚደርሰው ስደት ቀነሰ

  7. የካቲት 22, 2001—የጆርጂያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይሖዋ ምሥክሮችን ሕጋዊ ተቋማት እውቅና ሰረዘ፤ በወንድሞች ላይ የሚደርሰው ስደት ተፋፋመ

  8. ጥቅምት 17, 1999—በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የተደራጀ የቡድን ጥቃት መፈጸም ጀመረ፤ በግልዳኒ የጀመረው እንዲህ ያለው ጥቃት በመላው ጆርጂያ ተዛመተ

  9. ሚያዝያ 27, 1999—ጆርጂያ የአውሮፓ ምክር ቤት 41ኛ አባል አገር ሆነች

  10. ሰኔ 11, 1998—የይሖዋ ምሥክሮች በዩናይትድ ስቴትስ ያለው የዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ ኦቭ ፔንስልቬንያ ቅርንጫፍ በጆርጂያ ሕጋዊ ተቋም ሆኖ እንዲመዘገብ አደረጉ

  11. ሚያዝያ 17, 1998—የይሖዋ ምሥክሮች ጀሆቫስ ዊትነስስ ዩንየን የተባለውን ሕጋዊ ተቋም አስመዘገቡ

  12. 1969—የመጀመሪያው የይሖዋ ምሥክሮች ቡድን በተደራጀ መልኩ ስብሰባ ማድረግና መስበክ ጀመረ

  13. 1953—በናዚ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የይሖዋ ምሥክር የሆነች አንዲት የጆርጂያ ሶቪየት ሶሻሊስት ሪፑብሊክ ዜጋ፣ ወደ ጆርጂያ ተመልሳ ስለ እምነቷ መስበክ ጀመረች