ሰኔ 25, 2019
ጀርመን
በርሊን፣ ጀርመን—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከሰኔ 14-16, 2019
ቦታ፦ የበርሊን ኦሎምፒክ ስታዲየም፣ ጀርመን
ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ሩሲያኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 37,115
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 255
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,000
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ስሎቬንያ፣ ስካንዲኔቪያ፣ ብሪታንያ፣ ብራዚል፣ ኢኳዶር፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ፖላንድ
ተሞክሮ፦ ለስብሰባ የመጡት ልዑካን በርሊን የሚገኘውን ታዋቂውን የጴርጋሞን ሙዚየም ጎብኝተው ነበር። ወንድሞች ሙዚየሙን በጎበኙበት ወቅት ሲመለከታቸው የነበረ አንድ የጥበቃ ሠራተኛ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ብዙ ሰዎች እምነት ስለሌላቸው ተስፋ ቢስ ሆነዋል። እናንተ ግን እምነት እንዳላችሁና በመካከላችሁ ፍቅር እንዳለ በግልጽ ማየት ይቻላል። ሌላ የጥበቃ ሠራተኛ ደግሞ “እንደ እናንተ ያሉ ጎብኚዎች ሲመጡ ጊዜው በፍጥነት ነው የሚሄደው፤ ተጨማሪ ሰዓት በመሥራቴ ደስተኛ ነኝ” ብሏል።
የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች በአየር ማረፊያ ልዑካኑን ሲቀበሉ
ወንድሞችና እህቶች ስብሰባው በሚደረግበት ስታዲየም ግቢ ውስጥ ሲጨዋወቱ
ባሕላዊ ልብስ የለበሱ ልዑካን ፎቶግራፍ ሲነሱ
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ሳሙኤል ኸርድ የቅዳሜን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ
ልዑካኑ በእንግሊዝኛ የሚተላለፈውን ፕሮግራም እያዳመጡ ማስታወሻ ሲይዙ። ሁለት ተሰብሳቢዎች በሌላ ቋንቋ የሚተላለፈውን ፕሮግራም በጆሮ ማዳመጫ ሲከታተሉ
ወንድሞችና እህቶች ቅዳሜ የተከናወነውን የጥምቀት ሥነ ሥርዓት ሲከታተሉ
ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እሁድ ቀን ሕዝቡን ሲሰናበቱ
በ1936 ተገንብቶ የተጠናቀቀው የበርሊን ኦሎምፒክ ስታዲየም በመጀመሪያው የስብሰባ ቀን ላይ። ይህ ስታዲየም፣ በ1990 የበርሊን ግንብ ከፈረሰ በኋላ የተከናወነው ታሪካዊው የበርሊን ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ተደርጎበት ነበር
ልዑካኑ ከዝነኛው ብራንደንበርክ በር ፊት ለፊት በአደባባይ ምሥክርነት ሲካፈሉ
ልዑካኑ በጴርጋሞን ሙዚየም አቅራቢያ ተሰብስበው
ተመልካቾቹ ምሽት ላይ የነበረው ፕሮግራም ሲደመደም እያጨበጨቡ