ታኅሣሥ 14, 2021
ዩናይትድ ስቴትስ
በደቡብና በመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ የተከሰቱት አውሎ ነፋሶች ከባድ ውድመት አስከትለዋል
ከታኅሣሥ 10, 2021 ጀምሮ በተከታታይ የተከሰቱት ከባድ አውሎ ነፋሶች በደቡብና በመካከለኛው ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ስምንት ግዛቶችን መትተዋል፤ እንዲያውም አንዱ አውሎ ነፋስ 402 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ጉዳት አድርሷል። አውሎ ነፋሶቹ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፉ ከመሆኑም ሌላ ንብረት አውድመዋል። ከሁሉ የከፋው ጉዳት የደረሰበት የኬንተኪ ግዛት ነው።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ከወንድሞቻችን መካከል ጉዳት የደረሰበት ወይም የሞተ የለም
31 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
10 ቤቶች አነስተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል
3 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
9 ቤቶች ፈርሰዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾቹና የአካባቢው ሽማግሌዎች አውሎ ነፋሱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ ቤተሰቦችን እያጽናኑና እያበረታቱ ነው
የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው
ይሖዋ በእነዚህ የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ችግር ላይ ለወደቁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከልብ እንደሚራራላቸው እርግጠኞች ነን።—ኢሳይያስ 63:9