በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 14, 2025
ናይጄርያ

የማቴዎስ እና የማርቆስ መጻሕፍት በሃውሳ፣ በአቡዋ፣ በኦክፔ፣ በካና እና በጎካና ቋንቋዎች ወጡ

በርካታ የናይጄርያ ቋንቋዎች የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለንባብ አበቁ

በርካታ የናይጄርያ ቋንቋዎች የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለንባብ አበቁ

የካቲት 9, 2025 ኢጌዱማ በሚገኘው የናይጄርያ ቅርንጫፍ ቢሮ የተካሄደ ልዩ ስብሰባ ነበር። ፕሮግራሙን በአካል የታደሙት ተሰብሳቢዎች ብዛት 1,143 ነው፤ ሌሎች 579,436 ሰዎች ደግሞ በቅርንጫፍ ቢሮው ክልል ሥር ባሉ የጉባኤና የትላልቅ ስብሰባ አዳራሾች ውስጥ ሆነው ፕሮግራሙን በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ተከታትለዋል።

የናይጄርያ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ሳሙኤል ኦላንሬዋጁ ፕሮግራሙ ላይ እንዳበሰረው የማቴዎስ እና የማርቆስ መጻሕፍት በሃውሳ፣ በአቡዋ፣ በኦክፔ፣ በካና እና በጎካና ቋንቋዎች ወጥተዋል። በአካል ከታደሙት መካከል ከእነዚህ አምስት ቋንቋዎች አንዱን መናገር የሚችሉ ተሰብሳቢዎች በወረቀት የታተመውን የማቴዎስ መጽሐፍ ቅጂ አግኝተዋል። በዚሁ ፕሮግራም ላይ በፒጅን (ምዕራብ አፍሪካ) እና በኡሮቦ ቋንቋዎችም የተወሰኑ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ወጥተዋል። ሁሉም መጻሕፍት jw.org እና JW ላይብረሪ ላይ ወዲያውኑ ለንባብ በቅተዋል።

ናይጄርያ ውስጥ እነዚህን ሰባት ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎች ብዛት ከ100 ሚሊዮን በላይ ነው፤ ከእነዚህም መካከል 95,000 ገደማ የሚሆኑ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ይገኙበታል። በቀላሉ በሚገባ ቋንቋ የተተረጎሙትን እነዚህን መጻሕፍት በማግኘታቸው ተደስተዋል፤ በግል ጥናት፣ በጉባኤ ስብሰባዎችና በአገልግሎት ላይ ሊጠቀሙበት ጓጉተዋል።