የካቲት 10, 2021
ሩሲያ
ወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን የሰባት ዓመት ተኩል እስራት ተፈረደበት፤ በ2017 ከተጣለው እገዳ በኋላ ይህ እጅግ ከባዱ ቅጣት ነው
ዓርብ፣ የካቲት 10, 2021 ሩሲያ ውስጥ በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የአብንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በ63 ዓመቱ በወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን ላይ የሰባት ዓመት ተኩል እስራት ፈርዶበታል። ይህ ፍርድ ድርጅቱ 2017 ከታገደ በኋላ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ ከተጣሉት ቅጣቶች ሁሉ ከባዱ ነው።
ወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን ከሚያዝያ 23, 2020 ጀምሮ የወንጀል ክስ ተመሥርቶበት ነበር። ወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ሃይማኖታዊ አገልግሎት በማደራጀትና መንፈሳዊ መዝሙሮችን በመዘመር “ወንጀል” ክስ ተመሥርቶበት ነበር። ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የመጨረሻ ንግግር ላይ፣ እምነቱ የተመሠረተባቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎች በሚገባ አስረድቷል፤ እንዲህ ብሏል፦ “ክቡር ፍርድ ቤት ሕይወቴን የምመራው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኙት መመሪያዎች ነው፤ በእነዚህ መመሪያዎች ውስጥ ደግሞ ጽንፈኝነትም ሆነ ጥላቻ ፈጽሞ አይገኝም።”