መስከረም 20, 2023
ሩሲያ
ወንድም ማክሲም ቤልቲኮቭ ከእስር ተፈታ
ወንድም ማክሲም ቤልቲኮቭ መስከረም 15, 2023 በኻድይዥንስክ ከሚገኝ የሩሲያ እስር ቤት ተፈትቷል። ጥፋተኛ ነው ተብሎ የሁለት ዓመት እስራት የተፈረደበት ጥር 17, 2022 ነበር። ማረፊያ ቤት የቆየበት ጊዜ ታሳቢ ስለተደረገ የእስር ጊዜው መስከረም 15, 2023 ተጠናቅቋል።
ማክሲምና ባለቤቱ ማሪያ ሦስት ወንዶች ልጆች አሏቸው። ማክሲም በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት እንዲህ ብሎ ነበር፦ “እኔና ቤተሰቤ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ አዎንታዊ አመለካከት ይዘን መቀጠል የቻልነው ከይሖዋ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ምንም ነገር እንደሌለ እርግጠኞች ስለነበርን ነው። ምንም ነገር ቢፈጠር ልክ በኢያሱ 24:15 ላይ እንደተገለጸው ‘እኔና ቤተሰቤ ይሖዋን ለማገልገል’ ቆርጠናል።
ማክሲም በጽንፈኝነት ተከስሶ ፍርድ ፊት በቀረበበት ጊዜ ለችሎቱ እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፦ “እንደ ጽንፈኛ የሚያስቆጥር ምንም ነገር አላደረግሁም። እያደረግሁ ያለሁት ነገር ትክክል መሆኑን እርግጠኛ ነኝ፤ ስለዚህ አላፍርም ወይም አልሸማቀቅም። የይሖዋ ምሥክር በመሆኔ ምክንያት ፍርድ ፊት መቅረቤ ያኮራኛል።”
አሁን ማክሲም፣ ማሪያና ልጆቻቸው በድጋሚ አብረው መሆን ችለዋል። ይሖዋ እነሱን አብዝቶ መካረኩን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 4:3