የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በjw.org ላይ ጥሩ የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ኩኪዎችንና ሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። አንዳንድ ኩኪዎች ድረ ገጹ እንዲሠራ የግድ ስለሚያስፈልጉ መከልከል አይቻልም። አጠቃቀምህን ለማሻሻል ብቻ የምንጠቀምባቸውን ሌሎች ተጨማሪ ኩኪዎች መፍቀድ ወይም መከልከል ትችላለህ። ይህ መረጃ በፍጹም አይሸጥም ወይም ለንግድ ዓላማ አይውልም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ገጽ ተመልከት፦ የኩኪዎችንና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ዓለም አቀፍ ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ ምርጫዎችን ማስተካከል ከፈለግክ ይህን ገጽ ተጠቀም፦ የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ቼቹሊን እና ባለቤቱ ዬሌና

መጋቢት 19, 2024 | የታደሰው፦ የካቲት 19, 2025
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ባልና ሚስቱ ተፈረደባቸው | ‘የሚያጽናናኝ ይሖዋ ራሱ ነው’

ወቅታዊ መረጃ—ባልና ሚስቱ ተፈረደባቸው | ‘የሚያጽናናኝ ይሖዋ ራሱ ነው’

የካቲት 19, 2025 በካምቻትካ ግዛት የሚገኘው የፔትሮፓቭሎቭስክ ካምቻትስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሰርጌ ቼቹሊን እና ባለቤቱ እህት ዬሌና ቼቹሊና ጥፋተኛ ናቸው በማለት እያንዳንዳቸው በስድስት ዓመት የገደብ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። አሁን እስር ቤት አይገቡም።

ጥቅምት 30, 2024 በቭላዲቮስቶክ የሚገኘው ዘጠነኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ ቼቹሊን እና በባለቤቱ በእህት ዬሌና ቼቹሊና ላይ ተላልፎ የነበረውን ፍርድ ሽሮታል። ክሳቸው በድጋሚ እንዲታይ ወደ መጀመሪያው ፍርድ ቤት ይመለሳል።

ሚያዝያ 22, 2024 በካምቻትካ ግዛት የሚገኘው የፔትሮፓቭሎቭስክ ካምቻትስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ ቼቹሊን እና በባለቤቱ በእህት ዬሌና ቼቹሊና ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሁለቱም የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። በአሁኑ ወቅት እስር ቤት አይገቡም።

አጭር መግለጫ

እንደ ሰርጌና ዬሌና ሁሉ እኛም ፍጹም የሆነውን የአምላክ ቃል ከፍ አድርገን እንመለከተዋለን፤ በፈተና ወቅት በታማኝነት መጽናት እንድንችል ኃይላችንን ያድስልናል እንዲሁም ጥበብ ይሰጠናል።​—መዝሙር 19:7

የክሱ ሂደት

  1. መስከረም 25, 2022

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  2. ጥቅምት 17, 2022

    ቤታቸው ተፈተሸ

  3. መስከረም 6, 2023

    ሰርጌ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  4. መስከረም 7, 2023

    ዬሌና የጉዞ ገደቦች ተጣሉባት

  5. ታኅሣሥ 26, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ