የካቲት 2, 2022
ማዳጋስካር
በማዳጋስካር የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ አስከተለ
ጥር 2022 በማዳጋስካር ዋና ከተማ በአንታናናሪቮ የጣለው ከባድ ዝናብ፣ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ያስከተለ ከመሆኑም ሌላ ለሕንፃዎች መደርመስ ምክንያት ሆኗል። በአካባቢው፣ ከባድ ዝናብ መጣሉን ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ከወንድሞቻችን እና ከእህቶቻችን መካከል አካላዊ ጉዳት የደረሰበት ወይም የሞተ የለም
ቢያንስ 693 የሚያህሉ አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽ የለም
የእርዳታ እንቅስቃሴ
ቅርንጫፍ ኮሚቴው የእርዳታ ሥራውን የሚያስተባብር የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሟል፤ ኮሚቴው ሥራውን የሚያከናውነው የኮቪድ-19 የደህንነት ደንቦችን ባገናዘበ መልኩ ነው
የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው የሚኖሩ የጉባኤ ሽማግሌዎች ለወንድሞቻችን መንፈሳዊ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም ጊዜያዊ መጠለያ፣ ምግብ እና ሌሎች የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማቅረብ ቁሳዊ እርዳታ እየሰጡ ነው
በዚህ ፈታኝ ጊዜ ይሖዋ ለወንድሞቻችን “የተመሸገ ስፍራ” መሆኑን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 31:2