ክርስቲያናዊ ሕይወት
ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ስለ አምላክ ዓላማዎች የሚገልጸውን እውነት ማወጅ አለብን። (ዮሐ 18:37) በተጨማሪም የምንኖረው በውሸትና በክፋት በተሞላ ዓለም ውስጥ ቢሆንም ከእውነት ጋር ደስ ሊለን፣ እውነት ልንናገር እንዲሁም እውነት የሆነውን ነገር ልናስብ ይገባል።—1ቆሮ 13:6፤ ፊልጵ 4:8
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
-
ሐሜትን ላለመስማትና ላለማሰራጨት ቁርጥ ውሳኔ አድርግ።—1ተሰ 4:11
-
ሌሎች ጉዳት ሲደርስባቸው አትደሰት
-
አዎንታዊ በሆኑና በሚያበረታቱ ነገሮች ተደሰት
“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—በዓመፅ ሳይሆን ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ዴቢ ‘በዓመፅ እንደተደሰተች’ የሚያሳየው ምንድን ነው?
-
አሊስ ከዴቢ ጋር ያደረገችው ጭውውት አዎንታዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ያደረገችው እንዴት ነው?
-
ከሌሎች ጋር ልናወራቸው የምንችላቸው አንዳንድ መልካም ነገሮች የትኞቹ ናቸው?