የመግቢያ ናሙናዎች
ንቁ!
ጥያቄ፦ ለአደጋ አስቀድሞ መዘጋጀት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ጥቅስ፦ ምሳሌ 27:12
አበርክት፦ ይህ መጽሔት አደጋ ከመከሰቱ በፊት፣ በአደጋው ወቅትና ከአደጋው በኋላ ምን እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብን ይገልጻል።
እውነትን አስተምሩ
ጥያቄ፦ አምላክን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ጥቅስ፦ 1ዮሐ 5:3
እውነት፦ አምላክን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው ትእዛዛቱን በመጠበቅ ነው።
የሞቱ ሰዎች እንደገና በሕይወት መኖር ይችላሉ? (T-35)
ጥያቄ፦ በርካታ ሰዎች የሞተባቸውን ሰው ለማሰብ ሲሉ የሟቹን ሙት ዓመት ያከብራሉ። በሞት የተለዩንን የምንወዳቸውን ሰዎች ዳግመኛ የምናገኛቸው ይመስልሃል?
ጥቅስ፦ ሥራ 24:15
አበርክት፦ ይህ ትራክት፣ የትንሣኤ ተስፋ ለአንተ ምን ጥቅም እንደሚያስገኝልህ ይገልጻል። [የሚቻል ከሆነ የሞቱ ሰዎች ሊነሱ ይችላሉ? የሚለውን ቪዲዮ አሳይ።]
የራስህን መግቢያ አዘጋጅ
ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።