ከጥር 3-9
መሳፍንት 15–16
መዝሙር 124 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ክህደት፣ እንዴት ያለ አሳፋሪ ድርጊት ነው!”፦ (10 ደቂቃ)
መንፈሳዊ ዕንቁዎች፦ (10 ደቂቃ)
መሳ 16:1-3—ሳምሶን ዝሙት አዳሪ ቤት የገባው ለምንድን ነው? (w05 3/15 27 አን. 6)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ) መሳ 16:18-31 (th ጥናት 10)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። መመሥከር፦ አምላክ ያስብልናል—ማቴ 10:29-31 የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ውይይቱ ቆም ሲል ቪዲዮውን አቁመህ በቪዲዮው ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ለአድማጮች አቅርብ።
መመሥከር፦ (3 ደቂቃ) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም። (th ጥናት 3)
መመሥከር፦ (5 ደቂቃ) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር አበርክት፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅ። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።) (th ጥናት 9)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
መጽሐፍ ቅዱስ ትዳራችንን ታድጎልናል፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ ቪዲዮው ላይ የታዩትን ባለትዳሮች ትዳራቸውን ለመታደግ የረዷቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው? ወደ ቀድሞው መንፈሳዊ ልማዳቸው ለመመለስ ጥረት ማድረጋቸው የጠቀማቸው እንዴት ነው? ባለትዳሮች በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ሲጥሩ ተስፋ መቁረጥ የሌለባቸው ለምንድን ነው? ባለትዳሮች መንፈሳዊ እርዳታ ከየት ማግኘት ይችላሉ?—ያዕ 5:14, 15
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) rr ምዕ. 18 አን. 9-15፣ ሣጥን 18ሀ
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 149 እና ጸሎት