በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ አጠቃላይ ሐሳቡን ለመረዳት ጥረት አድርጉ

መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ አጠቃላይ ሐሳቡን ለመረዳት ጥረት አድርጉ

የመጽሐፍ ቅዱስን ዘገባዎች ስታነቡ አጠቃላይ ሐሳቡን ለመረዳት ጥረት አድርጉ። የምንባቡን አውድ፣ በታሪኩ ውስጥ የተካተቱትን ሰዎችና ከወሰዱት እርምጃ በስተጀርባ ያለውን ምክንያት ለማወቅ ሞክሩ። በአካባቢው የነበረውን ሁኔታ ለማየት፣ ድምፆቹን ለመስማት፣ መዓዛውን ለማሽተት እንዲሁም የባለታሪኮቹን ስሜት ለመረዳት በዓይነ ሕሊናችሁ የመሣል ችሎታችሁን ተጠቀሙ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችሁ ጥልቀት ይኑረው—ተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • በዮሴፍና በወንድሞቹ መካከል ውጥረት እንዲፈጠር ያደረጉት አንዳንድ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

  • የዮሴፍ ወንድሞች ስሜታዊነት የሚንጸባረቅበት እርምጃ ይወስዱ የነበረው ለምን ሊሆን ይችላል?

  • የዮሴፍ አባት ስለሆነው ስለ ያዕቆብ ከቅዱሳን መጻሕፍት ምን መገንዘብ እንችላለን?

  • ያዕቆብ አለመግባባቶችን በመፍታት ረገድ ለልጆቹ ምን ግሩም ምሳሌ ትቶላቸዋል?

  • ከዚህ ቪዲዮ ምን ትምህርት አግኝተሃል?