ይሖዋ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል
ሴዴቅያስ፣ ይሖዋ ለባቢሎን እጁን እንዲሰጥ የሰጠውን መመሪያ አልታዘዘም
-
ሴዴቅያስ ዓይኑ እያየ ልጆቹ ተገደሉ። ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ዓይኑን አሳወረውና በመዳብ የእግር ብረት ታስሮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ፤ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በባቢሎን በእስር ቆይቷል
ኤቤድሜሌክ በይሖዋ ላይ ያለውን እምነትና ለነቢዩ ኤርምያስ ያለውን አሳቢነት አሳይቷል
-
ይሖዋ ይሁዳ በምትጠፋበት ወቅት ኤቤድሜሌክን እንደሚጠብቀው ቃል ገብቷል
ኤርምያስ ኢየሩሳሌም ከመጥፋቷ በፊት ለበርካታ ዓመታት በድፍረት ሰብኳል
-
ይሖዋ ኢየሩሳሌም በተከበበችበት ወቅት ኤርምያስን ጠብቆታል፤ እንዲሁም ባቢሎናውያን ከእስር እንዲፈቱት አድርጓል