ከግንቦት 5-11
ምሳሌ 12
መዝሙር 101 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. በትጋት መሥራት ብድራት ያስገኛል
(10 ደቂቃ)
ከንቱ ነገሮችን በማሳደድ ጊዜ አታባክኑ (ምሳሌ 12:11)
በትጋት ሥሩ፤ ታታሪ ሁኑ (ምሳሌ 12:24፤ w16.06 30 አን. 6)
በትጋት ለምታከናውኑት ሥራ ብድራት ታገኛላችሁ (ምሳሌ 12:14)
ጠቃሚ ምክር፦ ሥራችን ለሌሎች በሚያስገኘው ጥቅም ላይ ካተኮርን በትጋት በምናከናውነው ሥራ እርካታ እናገኛለን።—ሥራ 20:35፤ w15 2/1 5 አን. 4-6
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
ምሳሌ 12:16—በዚህ ጥቅስ ላይ ያለው መሠረታዊ ሥርዓት ችግር ሲያጋጥመን መንፈሰ ጠንካራ እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው? (ijwyp ርዕስ 95 አን. 10-11)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 12:1-20 (th ጥናት 5)
4. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)
5. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 4)
6. ተመላልሶ መጠየቅ
(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ልጆች ላሉት ሰው ድረ ገጻችንን አሳይ። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)
7. እምነታችንን ማብራራት
(3 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwfq ርዕስ 3—ጭብጥ፦ እውነተኛው ሃይማኖት የእናንተ ብቻ እንደሆነ ይሰማችኋል? (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)
መዝሙር 21
8. በይሖዋ እርዳታ የኢኮኖሚ ችግርን መቋቋም
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ሥራ ለማግኘት ተቸግረሃል? ሥራዬን አጣለሁ የሚል ስጋት አለብህ? አሊያም ደግሞ አሁን ወይም ዕድሜህ እየገፋ ሲሄድ ራስህን ለማስተዳደር እንደምትቸገር በማሰብ ትጨነቃለህ? የዚህ ዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓት አስተማማኝ አይደለም። ይሁንና ይሖዋ እሱን እስካስቀደምን ድረስ ድንገተኛ የኢኮኖሚ ችግር ቢያጋጥመንም እንኳ ምንጊዜም የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያሟላልን ቃል ገብቶልናል።—መዝ 46:1-3፤ 127:2፤ ማቴ 6:31-33
ይሖዋ ፈጽሞ አላሳፈረንም የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
-
ከወንድም አልቫራዶ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
1 ጢሞቴዎስ 5:8ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
-
ይህ ጥቅስ፣ ይሖዋ የቤተሰቡ አባላት የሆኑት አገልጋዮቹ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ምንጊዜም እንደሚያሟላላቸው ያላችሁን እምነት የሚያጠናክርላችሁ እንዴት ነው?
የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመቋቋም ሊረዱን የሚችሉ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን እስቲ እንመልከት፦
-
ኑሯችሁን ቀላል አድርጉ። አላስፈላጊ ዕዳን ወይም ወጪዎችን ቀንሱ።—ማቴ 6:22
-
ሥራና ትምህርት ስትመርጡ መንፈሳዊ ነገሮችን ለማስቀደም የሚያስችላችሁን ውሳኔ አድርጉ።—ፊልጵ 1:9-11
-
ትሑት ሁኑ፤ እንዲሁም እንደ ሁኔታው ማስተካከያ አድርጉ። ሥራ ካጣችሁ፣ የቤተሰባችሁን ፍላጎት ለማሟላት እስካስቻላችሁ ድረስ ዝቅ ተደርገው የሚታዩ ሥራዎችን ጨምሮ ሌሎች የሥራ መስኮችን ለመሞከር ፈቃደኞች ሁኑ።—ምሳሌ 14:23
-
ብዙ ቁሳዊ ነገር ባይኖራችሁም እንኳ ያላችሁን ነገር ለሌሎች ለማካፈል ፈቃደኞች ሁኑ።—ዕብ 13:16
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 26 አን. 1-8፣ በገጽ 204, 208 ላይ ያሉት ሣጥኖች