ከግንቦት 19-25
ምሳሌ 14
መዝሙር 89 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. አደጋ ሲከሰት አካሄዳችሁን አንድ በአንድ አጢኑ
(10 ደቂቃ)
“ቃልን ሁሉ” አትመኑ (ምሳሌ 14:15፤ w23.02 23 አን. 10-12)
በራሳችሁ ስሜት ወይም ተሞክሮ ብቻ አትመሩ (ምሳሌ 14:12)
ከይሖዋ ድርጅት የሚመጣውን መመሪያ የሚቃወሙ ሰዎችን አትስሙ (ምሳሌ 14:7)
ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ ሽማግሌዎች፣ አደጋ ሲከሰት መመሪያ ለመከተልና በይሖዋ ለመታመን ዝግጁ ናችሁ?—w24.07 5 አን. 11
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
ምሳሌ 14:17—“በጥሞና የሚያስብ ሰው አይወደድም” ሲባል ምን ማለት ሊሆን ይችላል? (w05 7/15 19 አን. 5-6)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 14:1-21 (th ጥናት 11)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የኢኮኖሚ ጉዳይ እንደሚያሳስበው ለነገረህ ሰው አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ አካፍል። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 3)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት የግለሰቡን ትኩረት ስቦት ስለነበረው ርዕሰ ጉዳይ የሚናገር መጽሔት አበርክት። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)
6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
(5 ደቂቃ) ጥናትህ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ እንዲያነብ አበረታታው፤ እንዲሁም ግቡ ላይ መድረስ የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (th ጥናት 19)
መዝሙር 126
7. ምንጊዜም ለአደጋ ዝግጁ ሁኑ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
በሽማግሌ የሚቀርብ። ቅርንጫፍ ቢሮው ወይም የሽማግሌዎች አካል የሰጡት ማሳሰቢያ ካለ ጥቀስ።
“በመጨረሻዎቹ ቀናት” ውስጥ ስንኖር ችግሮች እየተባባሱ እንደሚሄዱ እንጠብቃለን። (2ጢሞ 3:1፤ ማቴ 24:8) ብዙውን ጊዜ፣ አደጋ ሲከሰት የይሖዋ ሕዝቦች ወቅታዊና ሕይወት አድን የሆነ መመሪያ ይሰጣቸዋል። በዚያ ወቅት መትረፋችን የተመካው በአሁኑ ጊዜ በመንፈሳዊም ሆነ በቁሳዊ እንድንዘጋጅ የተሰጠንን መመሪያ በመታዘዛችን ላይ ሊሆን ይችላል።—ምሳሌ 14:6, 8
-
በመንፈሳዊ መዘጋጀት፦ ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ አዳብሩ። በተለያዩ የአገልግሎት መስኮች ያላችሁን ክህሎት አሳድጉ። ለተወሰነ ጊዜ ያህል ከጉባኤያችሁ ወንድሞች ለመነጠል ብትገደዱ አትሸበሩ። (ምሳሌ 14:30) ምንም ነገር ከይሖዋ አምላክና ከክርስቶስ ኢየሱስ ሊለያችሁ አይችልም።—od 176 አን. 15-17
-
በቁሳዊ መዘጋጀት፦ ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ቦርሳ ከማዘጋጀት በተጨማሪ እያንዳንዱ ቤተሰብ የተወሰነ ምግብ፣ ውኃ፣ መድኃኒትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ቤት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ አለበት፤ ምክንያቱም በአደጋው ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ ከቤት ሳይወጡ መቆየት ሊያስፈልግ ይችላል።—ምሳሌ 22:3፤ g17.5 4
አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
-
በአደጋ ጊዜ ይሖዋ የሚረዳን እንዴት ነው?
-
ለአደጋ ለመዘጋጀት የትኞቹን ተግባራዊ እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን?
-
በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 26 አን. 18-22፣ በገጽ 209 ላይ ያለው ሣጥን