ከሰኔ 9-15
ምሳሌ 17
መዝሙር 157 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. በትዳራችሁ ውስጥ ሰላም አስፍኑ
(10 ደቂቃ)
ሰላም ማስፈን ጥረት ይጠይቃል፤ ሆኖም ጥረቱ የሚክስ ነው (ምሳሌ 17:1፤ ሥዕሉን ተመልከት)
በጥቃቅን ጉዳዮች አትጨቃጨቁ (ምሳሌ 17:9፤ g 9/14 11 አን. 2)
ምንጊዜም ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ (ምሳሌ 17:14፤ w08 5/1 10 አን. 6–11 አን. 1)
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
ምሳሌ 17:24—ከዚህ ጥቅስ ምን ትምህርት እናገኛለን? (w06 9/15 19 አን. 9)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 17:1-17 (th ጥናት 10)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 5)
5. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 6 ነጥብ 4)
6. ንግግር
(5 ደቂቃ) ijwbv ርዕስ 60—ጭብጥ፦ የምሳሌ 17:17 ትርጉም ምንድን ነው? (th ጥናት 13)
መዝሙር 113
7. ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ለማድረግ የሚረዱ ልማዶችን አዳብሩ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ለአስደሳች የቤተሰብ ሕይወት ቁልፍ ነው። የቤተሰብ አባላት ግልጽ የሐሳብ ልውውጥ የሚያደርጉ ከሆነ ተባብረው በመሥራት ግቦቻቸውን ማሳካት እንዲሁም በአስቸጋሪ ጊዜያት እርስ በርስ መደጋገፍ ይችላሉ። (ምሳሌ 15:22) ታዲያ በቤተሰባችሁ ውስጥ ክፍት የሐሳብ ልውውጥ መስመር እንዲኖር ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?
አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ። (ዘዳ 6:6, 7) ቤተሰቦች አብረው ሲሠሩ፣ በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች አብረው ሲካፈሉ እንዲሁም አብረው ሲዝናኑ በመካከላቸው ጠንካራ ፍቅርና መተማመን ይመሠረታል። በተጨማሪም ዘና ብለው የሚጨዋወቱበት አጋጣሚ ያገኛሉ። አንዳንድ ጊዜ ሌሎቹ የቤተሰባችሁ አባላት ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር አብራችሁ ለማድረግ የራሳችሁን ምርጫ መሥዋዕት ማድረግ ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፤ ሆኖም እንዲህ ማድረጋችሁ አያስቆጭም፤ ምክንያቱም ዘላቂ ጥቅም ታገኛላችሁ። (ፊልጵ 2:3, 4) ይሁንና አብራችሁ የምታሳልፉትን ጊዜ በተሻለ መንገድ ልትጠቀሙበት የምትችሉት እንዴት ነው?—ኤፌ 5:15, 16
ሰላም ወደሰፈነበት የቤተሰብ ሕይወት የሚመራውን ካርታ ተከተሉ—ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ አድርጉ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
-
የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን አላግባብ መጠቀም ቤተሰቡ በሚያደርገው የሐሳብ ልውውጥ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል?
-
ከዚህ ቪዲዮ ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ ሌላስ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ጥሩ አድማጭ ሁኑ። (ያዕ 1:19) ልጆች፣ ወላጆቼ በተሳሳተ መንገድ ይረዱኛል ወይም ይቆጡኛል ብለው የማይፈሩ ከሆነ ሐሳባቸውን በነፃነት ለመግለጽ ሊነሳሱ ይችላሉ። ስለዚህ ልጆቻችሁ የሚናገሩት ነገር ቢረብሻችሁም እንኳ የተጋነነ ምላሽ እንዳትሰጡ ተጠንቀቁ። (ምሳሌ 17:27) ከዚህ ይልቅ በደንብ አዳምጧቸው፤ እንዲሁም ራሳችሁን በእነሱ ቦታ ለማስቀመጥ ጥረት አድርጉ። ሐሳባቸውንና ስሜታቸውን መረዳታችሁ ፍቅር በሚንጸባረቅበት መንገድ እነሱን ለማበረታታት ወይም ለመርዳት ያስችላችኋል።
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 27 አን. 19-22፣ በገጽ 212 ላይ ያለው ሣጥን