ክርስቲያናዊ ሕይወት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው
ኢየሱስ “በነፃ እንደተቀበላችሁ በነፃ ስጡ” በማለት አስተምሯል። (ማቴ 10:8) ይህን ግልጽ መመሪያ በመከተል መጽሐፍ ቅዱስን ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎቻችንን ለሰዎች የምናበረክተው ያለምንም ክፍያ ነው። (2ቆሮ 2:17) ይሁን እንጂ እነዚህ ጽሑፎች በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙ ውድ እውነቶችን ይዘዋል። በተጨማሪም ጽሑፎቻችንን ማተምና በዓለም ዙሪያ ወደሚገኙ ጉባኤዎች ማጓጓዝ ከፍተኛ ድካምና ወጪ ይጠይቃል። በመሆኑም መውሰድ ያለብን የሚያስፈልገንን ያህል ብቻ ነው።
በአደባባይ ምሥክርነትም ሆነ በሌላ የአገልግሎት መስክ በምንካፈልበት ወቅት ለሰዎች ጽሑፎችን ስንሰጥ አስተዋዮች መሆን ያስፈልገናል። (ማቴ 7:6) ለአላፊ አግዳሚው በሙሉ ጽሑፎቻችንን ዝም ብለን ከማደል ይልቅ ከሰዎቹ ጋር በመወያየት ፍላጎታቸውን ለማወቅ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። በዚህ ርዕስ ላይ በሚገኘው ሣጥን ውስጥ ከተጠቀሱት ጥያቄዎች መካከል ቢያንስ ለአንዱ ‘አዎ’ የሚል መልስ መስጠት ትችላለህ? ግለሰቡ ፍላጎት ይኖረው አይኑረው ማወቅ ካልቻልን ትራክት ብንሰጠው የተሻለ ይሆናል። እርግጥ ነው፣ ግለሰቡ መጽሔት ወይም ሌላ ጽሑፍ እንድንሰጠው ከጠየቀን በደስታ እንሰጠዋለን።—ምሳሌ 3:27, 28