በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጨረሻው እየቀረበ ሲመጣ ጸንታችሁ ቁሙ

መጨረሻው እየቀረበ ሲመጣ ጸንታችሁ ቁሙ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በቅርቡ የሚያጋጥሙን አስደናቂ ነገሮች ድፍረታችንንና በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ይፈትኑታል። የሐሰት ሃይማኖት ሲጠፋ ታላቁ መከራ ይጀምራል። (ማቴ 24:21፤ ራእይ 17:16, 17) ውጥረት በሚነግሥበት በዚያ ጊዜ ኃይለኛ የፍርድ መልእክት ማወጅ ሊኖርብን ይችላል። (ራእይ 16:21) የማጎጉ ጎግ ጥቃት ይሰነዝርብናል። (ሕዝ 38:10-12, 14-16) ይሖዋም ሕዝቡን ለመጠበቅ ሲል “ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን [የሚካሄደውን] ጦርነት” ይጀምራል። (ራእይ 16:14, 16) ወደፊት እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ደፋር ሆነን ለመገኘት በአሁኑ ጊዜ የእምነት ፈተናዎች ሲደርሱብን ጸንተን መቆም ይኖርብናል።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ላቅ ላሉት የይሖዋ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች በድፍረት ጥብቅና ቁሙ።—ኢሳ 5:20

  • ከእምነት ባልንጀሮቻችሁ ጋር በመሰብሰብ ይሖዋን ማምለካችሁን ቀጥሉ።—ዕብ 10:24, 25

  • ከይሖዋ ድርጅት የሚመጣውን መመሪያ ለመቀበል ፈጣን ሁኑ።—ዕብ 13:17

  • ይሖዋ በጥንት ዘመን ሕዝቦቹን ያዳነው እንዴት እንደሆነ አሰላስሉ።—2ጴጥ 2:9

  • ወደ ይሖዋ ጸልዩ፤ በእሱም ታመኑ።—መዝ 112:7, 8

ከፊታችን የሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶችተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አስፋፊዎቹ ጉባኤያቸው ከሌሎች ጉባኤዎች ጋር ሲዋሃድ ምን የታዛዥነት ፈተና አጋጠማቸው?

  • ድፍረትና ታዛዥነት ምን ተያያዥነት አላቸው?

  • አርማጌዶን ሲመጣ ድፍረት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

  • ከፊታችን ለሚጠብቁን ድፍረት የሚጠይቁ ክስተቶች ከአሁኑ ተዘጋጁ

    ይሖዋ ባለው የማዳን ኃይል ላይ ያለንን እምነት ለማጠናከር የሚረዳን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ የትኛው ነው?—2ዜና 20:1-24