በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሕዝቅኤል 28-31

ይሖዋ አንድ አረማዊ ብሔር ላደረገው ነገር ወሮታ ከፍሏል

ይሖዋ አንድ አረማዊ ብሔር ላደረገው ነገር ወሮታ ከፍሏል

29:18-20

ይሖዋ አንድ አረማዊ ብሔር ላደረገው ነገር ወሮታ የሚከፍል ከሆነ ታማኝ አገልጋዮቹ የሚያከናውኑትን ሥራ ደግሞ ይበልጥ ከፍ አድርጎ እንደሚመለከት ምንም ጥርጥር የለውም!

ባቢሎናውያን ምን አድርገዋል?

ጢሮስን ከበዋል

እኔ ምን እያደረግኩ ነው?

ምን ዓይነት መንፈሳዊ ውጊያ በማድረግ ላይ ነኝ?

ባቢሎናውያን ምን መሥዋዕት ከፍለዋል?

  • ጢሮስን ለ13 ዓመታት ከበው መቆየታቸው ብዙ ወጪ አስወጥቷቸዋል

  • ባቢሎናውያን ወታደሮች አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • ባቢሎናውያን ላደረጉት ነገር ምንም ዋጋ አልተከፈላቸውም

ምን መሥዋዕት እየከፈልኩ ነው?

ይሖዋን ለማገልገል ስል ምን መሥዋዕት ከፍያለሁ?

ይሖዋ ለባቢሎናውያን ወሮታ የከፈለው በምን መንገድ ነው?

ይሖዋ የግብፅን ሀብት እንዲበዘብዙ ፈቅዶላቸዋል

ከይሖዋ የማገኘው ወሮታ ምንድን ነው?

ይሖዋ ወሮታ የሚከፍለኝ እንዴት ነው?