ክርስቲያናዊ ሕይወት
በቅርቡ ረዳት አቅኚ መሆን የምችለው መቼ ነው?
ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ያየው ራእይ የይሖዋ ሕዝቦች በፈቃደኝነት መሥዋዕት እንደሚያቀርቡ ያሳያል። የምሥጋና መሥዋዕት በማቅረብ ረገድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት የምንችለው እንዴት ነው?—ዕብ 13:15, 16
ይህን ማድረግ የሚቻልበት አንዱ መንገድ ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል ነው። በ2018 የአገልግሎት ዓመት ውስጥ አምስት ቅዳሜ ወይም አምስት እሁድ ያላቸው በርካታ ወራት አሉ። ይህም በተለይ የሙሉ ጊዜ ሰብዓዊ ሥራ ለሚሠሩና አብዛኛውን ጊዜ ቅዳሜና እሁድ ብቻ አገልግሎት ለሚወጡ አስፋፊዎች ጠቃሚ ነው። ከዚህም በተጨማሪ አስፋፊዎች በመጋቢትና በሚያዝያ ወራት፣ እንዲሁም የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን በሚጎበኝበት ወር ከ30 ወይም ከ50 ሰዓት አንዱን በመምረጥ ረዳት አቅኚ ሆነው ማገልገል ይችላሉ።
ሁኔታችን ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል የማይፈቅድልን ቢሆንስ? የአገልግሎታችንን ጥራት፣ ከተቻለ ደግሞ መጠኑን ከፍ ለማድረግ ጥረት ማድረግ እንችላለን። ሁኔታችን ምንም ይሁን ምን፣ ለይሖዋ ያለን ፍቅር በ2018 የአገልግሎት ዓመት ለእሱ ምርጣችንን እንድንሰጠው እንዲያነሳሳን ምኞታችን ነው!—ሆሴዕ 14:2
በይሖዋ እርዳታ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ሳቢና በይሖዋ አገልግሎት የምታደርገውን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ያነሳሳት ምንድን ነው?
-
ሳቢና የተወችው ምሳሌ አንተን የሚያበረታታህ እንዴት ነው?
-
በ2018 የአገልግሎት ዓመት ረዳት አቅኚ ሆነህ ማገልገል የምትችለው በየትኞቹ ወራት ነው?