በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | የሐዋርያት ሥራ 6-8

አዲስ የተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ ተፈተነ

አዲስ የተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ ተፈተነ

6:1-7፤ 7:58–8:1

ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑና በቅርቡ የተጠመቁ መበለቶች በኢየሩሳሌም በቆዩበት ወቅት መድልዎ ደርሶባቸው ነበር። ታዲያ እነዚህ መበለቶች በዚህ ተሰናከሉ ወይስ ይሖዋ ነገሮችን እስኪያስተካክል በትዕግሥት ጠበቁ?

እስጢፋኖስ በድንጋይ ከተወገረ በኋላ በተነሳው ከባድ ስደት ምክንያት በኢየሩሳሌም የነበሩት ክርስቲያኖች በይሁዳና በሰማርያ ክልሎች ሁሉ ተበተኑ፤ ታዲያ እነዚያ ክርስቲያኖች የአገልግሎት ቅንዓታቸው ቀዝቅዞ ነበር?

አዲስ የተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ የይሖዋ ድጋፍ ስላልተለየው ወንድሞች የደረሰባቸውን ፈተና በጽናት የተቋቋሙ ከመሆኑም ሌላ በቁጥር እየጨመሩ ሄደዋል።—ሥራ 6:7፤ 8:4

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘ፈተናዎች ሲያጋጥሙኝ ምን አደርጋለሁ?’