በጆርጂያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ደስተኛ ቤተሰብ የተባለውን ብሮሹር ሲያበረክቱ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ኅዳር 2017

የመግቢያ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ መጽሔትን ለማበርከትና ስለ አምላክ ስም እውነቱን ለማስተማር የተዘጋጁ የመግቢያ ናሙናዎች። የመግቢያ ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“ይሖዋን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ”

አምላክን መፈለግ ሲባል ምን ማለት ነው? ይሖዋን ሳይፈልጉ ከቀሩት እስራኤላውያን ምን እንማራለን?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ

ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ረገድ ውጤታማ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? የሰዎቹን ፍላጎት ለማሳደግ ምንጊዜም ጥረት አድርግ፤ በእያንዳንዱ ተመላልሶ መጠየቅ ወቅት አንድ ግብ ለማሳካት ሞክር እንዲሁም ዋናው ግብህ ምን እንደሆነ ምንጊዜም አትዘንጋ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ከስህተታችሁ ተማሩ

ስህተት በምንሠራበት ጊዜ ይሖዋ፣ መስተካከል እንደማንችል አድርጎ በማሰብ ተስፋ እንደማይቆርጥብን የዮናስ ታሪክ ያሳያል። ሆኖም ይሖዋ ከስህተታችን እንድንማርና አስፈላጊውን ለውጥ እንድናደርግ ይጠብቅብናል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ከዮናስ መጽሐፍ የምናገኛቸው ትምህርቶች

በዮናስ ታሪክ ላይ ማሰላሰላችን ተስፋ የሚያስቆርጡ ሁኔታዎችን እንድንቋቋም፣ ለአገልግሎት ክልላችን አሉታዊ አመለካከት እንዳይኖረን እንዲሁም በጸሎት አማካኝነት ማጽናኛ እንድናገኝ ሊረዳን ይችላል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?

ከመንፈሳዊ ወንድሞቻችን ጋር ያለን ግንኙነት ለይሖዋ ከምናቀርበው አምልኮ ጋር ምን ተያያዥነት አለው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ ሁኑ

ባቢሎናውያን፣ ይሁዳን እንደሚያጠፏት የተነገረው ትንቢት የሚፈጸም አይመስልም ነበር። ያም ቢሆን ይሖዋ የተናገረው ትንቢት መፈጸሙ የማይቀር ነበር፤ በመሆኑም ዕንባቆም ትንቢቱ የሚፈጸምበትን ጊዜ በተስፋ መጠባበቅ ነበረበት።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሁኔታችሁ ቢለወጥም ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ ሁኑ

ያጋጠመን ለውጥ በአምልኳችንና ከይሖዋ ጋር ባለን ዝምድና ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፤ ታዲያ በዚህ ወቅት ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ ሆነን ለመኖር ምን ሊረዳን ይችላል?