የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በjw.org ላይ ጥሩ የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ኩኪዎችንና ሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። አንዳንድ ኩኪዎች ድረ ገጹ እንዲሠራ የግድ ስለሚያስፈልጉ መከልከል አይቻልም። አጠቃቀምህን ለማሻሻል ብቻ የምንጠቀምባቸውን ሌሎች ተጨማሪ ኩኪዎች መፍቀድ ወይም መከልከል ትችላለህ። ይህ መረጃ በፍጹም አይሸጥም ወይም ለንግድ ዓላማ አይውልም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ገጽ ተመልከት፦ የኩኪዎችንና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ዓለም አቀፍ ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ ምርጫዎችን ማስተካከል ከፈለግክ ይህን ገጽ ተጠቀም፦ የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አንዲት በዕድሜ የገፉ እህት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ባለ የመዋጮ ሣጥን ውስጥ መዋጮ ሲያደርጉ። ምስሎች፦ 1. ወንድሞችና እህቶች በግንባታ ፕሮጀክት ሲካፈሉ። 2. የJW ብሮድካስቲንግ ፕሮግራም። 3. ወንድሞችና እህቶች የእርዳታ ቁሳቁሶችን ከመኪና ላይ ሲያወርዱ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ”

“የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ”

የፈቃደኝነት መዋጮ፣ ትዝ ሲለን ብቻ የምናደርገው ነገር መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳሳሰበው በቋሚነት ‘የተወሰነ ገንዘብ ማስቀመጥ’ ይኖርብናል። (1ቆሮ 16:2) በመንፈስ መሪነት የተሰጠውን ይህን ምክር መከተላችን ንጹሑን አምልኮ ለመደገፍና ደስታ ለማግኘት ያስችለናል። የምናደርገው መዋጮ ለእኛ የቱንም ያህል ጥቂት መስሎ ቢታየን፣ ይሖዋ ባሉን ውድ ነገሮች እሱን ለማክበር ያለንን ፍላጎት በእጅጉ ያደንቃል።—ምሳሌ 3:9

የተወሰነ ገንዘብ ስላስቀመጣችሁ እናመሰግናችኋለን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • መዋጮ የምናደርገውን ገንዘብ አስቀድመን ማቀዳችን ምን ጥቅሞች አሉት?

  • አንዳንዶች ‘የተወሰነ ገንዘብ ለማስቀመጥ’ የትኞቹን ዘዴዎች ይጠቀማሉ?