ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ በገባው ቃል ላይ ያለህ እምነት ምን ያህል ጠንካራ ነው?
ኢያሱም ሆነ ሰለሞን፣ ይሖዋ ከሰጠው ተስፋ ውስጥ ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል እንደሌለ መሥክረዋል። (ኢያሱ 23:14፤ 1ነገ 8:56) እምነት የሚጣልባቸው የእነዚህ ሁለት ሰዎች ምሥክርነት፣ እምነታችንን ይበልጥ ያጠናክርልናል።—2ቆሮ 13:1፤ ቲቶ 1:2
በኢያሱ ዘመን፣ ይሖዋ የገባውን ቃል የፈጸመው እንዴት ነው? “ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል የለም” የተባለውን ድራማ በቤተሰብ ሆናችሁ ተመልከቱ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ (1) በሥራ የተደገፈ እምነት ያሳየችውን ረዓብን መምሰል የምትችሉት እንዴት ነው? (ዕብ 11:31፤ ያዕ 2:24-26) (2) የአካን ታሪክ፣ ሆን ብሎ ትእዛዝ መጣስ ጥፋት እንደሚያስከትል የሚያሳየው እንዴት ነው? (3) ገባኦናውያን ደፋር ተዋጊዎች ቢሆኑም ኢያሱን በማታለል ከእስራኤላውያን ጋር ሰላም የፈጠሩት ለምንድን ነው? (4) አምስት የአሞራውያን ነገሥታት በእስራኤላውያን ላይ በተነሱ ጊዜ የይሖዋ ቃል የተፈጸመው እንዴት ነው? (ኢያሱ 10:5-14) (5) የአምላክን መንግሥትና ጽድቁን በሕይወታችሁ ውስጥ ስታስቀድሙ ይሖዋ ምን አድርጎላችኋል?—ማቴ 6:33
ይሖዋ እስካሁን ባከናወናቸው፣ እያከናወናቸው ባለውና ወደፊት በሚያከናውናቸው ነገሮች ላይ ማሰላሰላችን፣ እሱ በገባው ቃል ላይ ያለንን እምነት ይበልጥ ያጠናክርልናል።—ሮም 8:31, 32