በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መስበክና ማስተማር—ደቀ መዛሙርት ለማድረግ የሚረዱ ወሳኝ ነገሮች

መስበክና ማስተማር—ደቀ መዛሙርት ለማድረግ የሚረዱ ወሳኝ ነገሮች

ኢየሱስ ሄደው ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ ተከታዮቹን አዟቸዋል። (ማቴ 28:19) ይህም መስበክን እና ማስተማርን ይጨምራል። በመሆኑም ‘ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ወሳኝ ሚና በሚጫወቱት በእነዚህ ሁለት መስኮች ያለኝን ችሎታ ማሳደግ የምችለው እንዴት ነው?’ በማለት አልፎ አልፎ ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል።

መስበክ

ሰዎች ወደ እኛ እንዲመጡ ከመጠበቅ ይልቅ “መስማት የሚገባውን ሰው” ለማግኘት በትጋት መፈለግ አለብን። (ማቴ 10:11) በአገልግሎት ላይ ‘ከምናገኛቸው ሰዎች ጋር’ ውይይት ለመጀመር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን በንቃት እንከታተላለን? (ሥራ 17:17) ሊዲያ ደቀ መዝሙር የሆነችው ሐዋርያው ጳውሎስ ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት ነው።—ሥራ 16:13-15

“በማለዳ ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ እጅህ ሥራ አይፍታ” (መክ 11:6)

“ያለማሰለስ” መስበካችሁን ቀጥሉ—መደበኛ ባልሆነ መንገድ እና ከቤት ወደ ቤት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦

  • ሳሙኤል የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ሲያከናውን የእውነትን ዘር ለመዝራት የሚያስችለውን አጋጣሚ በንቃት ይከታተል እንደነበር ያሳየው እንዴት ነው?

  • በሁሉም የስብከት ዘዴዎች ለመካፈል ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

  • የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችሁን ስታከናውኑ የመንግሥቱን መልእክት ለማን መንገር ትችላላችሁ?

ማስተማር

ሰዎችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ ጽሑፍ ሰጥተናቸው ከመሄድ ያለፈ ነገር ማድረግን ይጠይቃል። መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ ለመርዳት ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግና ጥናት ማስጠናት ይኖርብናል። (1ቆሮ 3:6-9) ሆኖም የመንግሥቱን መልእክት ለሰዎች ለመንገር ያደረግነው ጥረት ያሰብነውን ያህል ውጤት ባያስገኝስ? (ማቴ 13:19-22) እንደ “ጥሩ አፈር” የሆነ ልብ ያላቸውን ሰዎች እስክናገኝ ድረስ ፍለጋችንን መቀጠል ይኖርብናል።—ማቴ 13:23፤ ሥራ 13:48

“እኔ ተከልኩ፤ አጵሎስ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን አምላክ ነው” (1ቆሮ 3:6)

“ያለማሰለስ” መስበካችሁን ቀጥሉ—በአደባባይ እና ደቀ መዛሙርት በማድረግ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦

  • ሰለሞንና ሜሪ በሕዝቅኤልና በአቢጋኤል ልብ ውስጥ የተዘራውን የእውነት ዘር ውኃ ያጠጡት እንዴት ነው?

  • በአደባባይ ምሥክርነትም ሆነ በሌሎች የአገልግሎት መስኮች ስንካፈል ግባችን ምን መሆን ይኖርበታል?

  • እውነትን ለሌሎች ለማስተማሩ ሥራ ትልቅ ቦታ እንደምንሰጥ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?