በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 12–16

እስራኤል ይሖዋን ረስቷል

እስራኤል ይሖዋን ረስቷል

ይሖዋ የይሁዳን ኩራትና የኢየሩሳሌምን እብሪት ለማጥፋት ውሳኔ አድርጎ ነበር፤ ኤርምያስ ይህን ጥፋት በምሳሌ ማሳየትን የሚጠይቅ ተፈታታኝ ተልእኮ ተሰጥቶት ነበር

ኤርምያስ ከተልባ እግር የተሠራ ቀበቶ ገዛ

13:1, 2

  • ቀበቶ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ ሁሉ የእስራኤል ብሔርም በምሳሌያዊ ሁኔታ ከይሖዋ ጋር መጣበቅ ይችል ነበር

ኤርምያስ ቀበቶውን ይዞ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሄደ

13:3-5

  • ቀበቶውን በቋጥኝ ስንጥቅ ውስጥ ከደበቀው በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ

ኤርምያስ ቀበቶውን ለማምጣት ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተመልሶ ሄደ

13:6, 7

  • ቀበቶው ተበላሽቶ አገኘው

ኤርምያስ ተልእኮውን ከተወጣ በኋላ ይሖዋ ስለ ጉዳዩ አብራራለት

13:8-11

  • ኤርምያስ ያደረገው ነገር ምንም ጥቅም የሌለው ሊመስል ቢችልም በፈቃደኝነት ታዟል፤ እንዲህ ማድረጉ ይሖዋ የሕዝቡን ልብ ለመንካት ባደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አስችሎታል