በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከሚያዝያ 8-14

መዝሙር 26–28

ከሚያዝያ 8-14

መዝሙር 34 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ዳዊት ንጹሕ አቋሙን ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት ያጠናከረው እንዴት ነው?

(10 ደቂቃ)

ዳዊት ይሖዋ እንዲያጠራው ጠይቋል (መዝ 26:1, 2w04 12/1 14 አን. 8-9)

ዳዊት ከመጥፎ ጓደኞች ርቋል (መዝ 26:4, 5w04 12/1 15 አን. 12-13)

ዳዊት የይሖዋን አምልኮ ይወድ ነበር (መዝ 26:8w04 12/1 16 አን. 17-18)


ዳዊት ስህተት የሠራባቸው ጊዜያት ቢኖሩም “በንጹሕ ልብ” ተመላልሷል። (1ነገ 9:4) ዳዊት ይሖዋን በሙሉ ልቡ ይወድና ያገለግል የነበረ መሆኑ ንጹሕ አቋም እንደነበረው ያሳያል።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 27:10—የቅርብ ጓደኞቻችን እንደተዉን ሲሰማን ይህ ጥቅስ የሚያጽናናን እንዴት ነው? (w06 7/15 28 አን. 15)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 27:1-14 (th ጥናት 2)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ ትራክት ተጠቀም። (th ጥናት 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ባበረከትከው ትራክት የጀርባ ገጽ ላይ በሚገኘው ጥያቄ ላይ ተወያዩ። ስለ jw.org ንገረው፤ ከዚያም በድረ ገጹ ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ነገሮች አሳየው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 3—ጭብጥ፦ የተበላሸው የምድር ሥነ ምህዳር ይስተካከላል። (th ጥናት 13)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 128

7. ንጹሕ የሥነ ምግባር አቋም ያላቸው ወጣቶች

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ክርስቲያን ወጣቶች የሥነ ምግባር ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ መታገል ያስፈልጋቸዋል። ፍጹም ካልሆነው ሥጋቸው ጋር ይታገላሉ፤ በተጨማሪም በአፍላ የጉርምስና ዕድሜ ላይ ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፤ በዚህ ዕድሜ ላይ የፆታ ስሜት ስለሚያይል የማመዛዝን ችሎታቸውን ሊያዛባው ይችላል። (ሮም 7:21፤ 1ቆሮ 7:36) ከዚህም ሌላ እኩዮቻቸው ተቃራኒም ሆነ ተመሳሳይ ፆታ ካላቸው ሰዎች ጋር የፆታ ብልግና እንዲፈጽሙ የማያባራ ተጽዕኖ ያሳድሩባቸዋል። (ኤፌ 2:2) ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁ ወጣቶቻችንን እንኮራባቸዋለን።

የወጣትነት ሕይወቴ—ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት እንድፈጽም የሚደረግብኝን ጫና መቋቋም የምችለው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ኮሪ እና ካምሪን ምን ዓይነት የእኩዮች ተጽዕኖ አጋጥሟቸዋል?

  • ንጹሕ አቋማቸውን እንዲጠብቁ የረዳቸው ምንድን ነው?

  • አንተስ ተመሳሳይ ሁኔታ ቢያጋጥምህ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊረዱህ ይችላሉ?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 8 አን. 5-12

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 38 እና ጸሎት