በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከሚያዝያ 1-7

መዝሙር 23–25

ከሚያዝያ 1-7

መዝሙር 4 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “ይሖዋ እረኛዬ ነው”

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ይመራናል (መዝ 23:1-3w11 5/1 31 አን. 3)

ይሖዋ ይጠብቀናል (መዝ 23:4w11 5/1 31 አን. 4)

ይሖዋ ይመግበናል (መዝ 23:5w11 5/1 31 አን. 5)

ጎበዝ እረኛ በጎቹን እንደሚንከባከብ ሁሉ ይሖዋም አገልጋዮቹን ይንከባከባል።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ የተንከባከበኝ እንዴት ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 23:3—‘የጽድቅ መንገድ’ ምንድን ነው? ከዚህ መንገድ እንዳንወጣስ ምን ይረዳናል? (w11 2/15 24 አን. 1-3)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የምድራችን ሥነ ምህዳር ጉዳይ ያሳስበኛል ለሚል ሰው አበረታች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አንብብ። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለው ብሮሹር ለተበረከተለት ሰው መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 54

7. የእንግዳ ሰዎችን ድምፅ አንሰማም

(15 ደቂቃ) ውይይት።

በጎች የእረኛቸውን ድምፅ ስለሚያውቁ ይከተሉታል። ድምፁን ከማያውቁት እንግዳ ሰው ግን ይሸሻሉ። (ዮሐ 10:5) እኛም በተመሳሳይ፣ አፍቃሪና እምነት የሚጣልባቸው እረኞቻችን የሆኑትን የይሖዋንና የኢየሱስን ድምፅ እንሰማለን። (መዝ 23:1፤ ዮሐ 10:11) “አስመሳይ ቃላት” በመናገር እምነታችንን ለማዳከም ከሚሞክሩት እንግዳ ሰዎች ድምፅ ደግሞ እንርቃለን።—2ጴጥ 2:1, 3

ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 በምድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንግዳ ድምፅ ስለተሰማበት ወቅት ይናገራል። ሰይጣን እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ ሔዋንን በማነጋገር አታሏታል። ለእሷ የሚያስብ መስሎ በመቅረብ ይሖዋ ስለተናገራቸው ቃላትና ስለ ማንነቱ ውሸት ተናግሯል። የሚያሳዝነው፣ ሔዋን ሰማችው። ይህም በእሷም ሆነ በቤተሰቧ ላይ ይህ ነው የማይባል መከራ አምጥቷል።

በዛሬው ጊዜም ሰይጣን አሉታዊ ዘገባዎችን፣ ከፊል እውነትነት ያላቸውን መረጃዎች አልፎ ተርፎም ዓይን ያወጡ ውሸቶችን በማናፈስ በይሖዋና በድርጅቱ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርብን ለማድረግ ይሞክራል። እንግዳ ድምፅ ስንሰማ መሸሽ ይኖርብናል። በማወቅ ጉጉት ተነሳስተን ለቅጽበትም እንኳ እንግዳ ድምፆችን ማዳመጥ በጣም አደገኛ ነው። ሰይጣን ከሔዋን ጋር ባደረገው አጭር ውይይት ወቅት እሷን ያታለላት ስንት ቃላትን ተጠቅሞ ነው? (ዘፍ 3:1, 4, 5) ይሁንና የምናውቀው እንዲሁም የሚወደንና የሚያስብልን ሰው ስለ ይሖዋ ድርጅት አሉታዊ ነገር ሊነግረን ቢሞክር ምን ማድረግ ይኖርብናል?

‘የእንግዳ ሰዎችን ድምፅ’ አትስሙ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

ጄድ አማኝ ካልሆነችው እናቷ ጋር በተያያዘ ያጋጠማትን ሁኔታ ከያዘችበት መንገድ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 55 እና ጸሎት