በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዮሐንስ 3-4

ኢየሱስ ለአንዲት ሳምራዊት ሴት መሠከረ

ኢየሱስ ለአንዲት ሳምራዊት ሴት መሠከረ

4:6-26, 39-41

ኢየሱስን መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲመሠክር ያስቻለው ምንድን ነው?

  • 4:7—ውይይቱን የጀመረው ስለ አምላክ መንግሥት በመናገር ወይም መሲሕ እንደሆነ በመግለጽ ሳይሆን ሴትየዋ ውኃ እንድትሰጠው በመጠየቅ ነው

  • 4:9—በዘሯ ምክንያት ስለ ሳምራዊቷ ሴት አሉታዊ አመለካከት አላደረበትም

  • 4:9, 12—ሴትየዋ ሊያወዛግቡ የሚችሉ ጉዳዮችን ብታነሳም ኢየሱስ ውይይቱ መስመሩን እንዳይስት አድርጓል።—cf ገጽ 77 አን. 3

  • 4:10—ከሴትየዋ የዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር የተያያዘ ምሳሌ በመጠቀም ውይይቱን ጀምሯል

  • 4:16-19—ሥነ ምግባር የጎደለው ሕይወት የምትመራ ቢሆንም ኢየሱስ በአክብሮት አነጋግሯታል

ይህ ዘገባ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመመሥከርን አስፈላጊነት የሚያሳየው እንዴት ነው?