ክርስቲያናዊ ሕይወት
ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት
በድርጊታችን (ፊልጵ 1:27)፦
-
ቤታቸውን አጮልቀን ለማየት ባለመሞከር የግለሰቦቹን ነፃነት እንደምናከብር እናሳይ። በሩ ላይ ቆመን መብላት፣ መጠጣት፣ ስልክ መደወል ወይም የጽሑፍ መልእክት መላክ የለብንም
በንግግራችን (ኤፌ 4:29)፦
-
በሩ እስኪከፈት ስንጠብቅ የቤቱ ባለቤት አጠገባችን ቢሆን የማንናገረውን ምንም ነገር መናገር የለብንም። እንዲያውም አንዳንድ አስፋፊዎች የቤቱ ባለቤት በሩን እስኪከፈትላቸው ድረስ ከአገልግሎት ጓደኛቸው ጋር የሚያደርጉትን ጭውውት ያቆማሉ፤ ይህም ቀጥሎ የሚናገሩትን ለመዘጋጀት ያስችላቸዋል