ከነሐሴ 5-11
መዝሙር 70–72
መዝሙር 59 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “ለቀጣዩ ትውልድ” ስለ አምላክ ኃይል ተናገሩ
(10 ደቂቃ)
ዳዊት በወጣትነቱ የይሖዋን ጥበቃ አግኝቷል (መዝ 71:5፤ w99 9/1 18 አን. 17)
ዳዊት በስተ እርጅናው የይሖዋን ድጋፍ አጣጥሟል (መዝ 71:9፤ g04 10/8 23 አን. 3)
ዳዊት ተሞክሮውን በመናገር ወጣቶችን አበረታቷል (መዝ 71:17, 18፤ w14 1/15 23 አን. 4-5)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በቤተሰብ አምልኳችን ላይ በጉባኤያችን ውስጥ ካሉት ለረጅም ጊዜ ይሖዋን ያገለገሉ ክርስቲያኖች መካከል ለማን ቃለ መጠይቅ ማድረግ እችላለሁ?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
መዝ 72:8—ይሖዋ በዘፍጥረት 15:18 ላይ ለአብርሃም የገባው ቃል በንጉሥ ሰለሞን የግዛት ዘመን ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (it-1 768)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መዝ 71:1-24 (th ጥናት 5)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መከራከር ሲጀምር ውይይቱን አዎንታዊ በሆነ መንገድ አቁም። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 5)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ከአንድ ዘመድህ ጋር ቀደም ሲል የጀመርከውን ውይይት ቀጥል፤ ግለሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመር እያመነታ ነው። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 4)
6. እምነታችንን ማብራራት
መዝሙር 76
7. ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆኑ ሐሳቦች
(15 ደቂቃ) ውይይት።
የቤተሰብ አምልኮ፣ ልጆች ስለ “ይሖዋ ተግሣጽና ምክር” የሚማሩበት ግሩም አጋጣሚ ይፈጥራል። (ኤፌ 6:4) መማር ሥራ ይጠይቃል፤ ሆኖም በተለይ ልጆች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ጉጉት እያዳበሩ ሲሄዱ መማር አስደሳች ሊሆንላቸው ይችላል። (ዮሐ 6:27፤ 1ጴጥ 2:2) ወላጆች የቤተሰብ አምልኳቸውን ትምህርት ሰጪና አስደሳች እንዲያደርጉ ለመርዳት የተዘጋጀውን “ ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆኑ ሐሳቦች” የሚለውን ሣጥን ከልስ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
-
ከእነዚህ ሐሳቦች መካከል የትኛውን መሞከር ትፈልጋላችሁ?
-
ጠቃሚ ሆኖ ያገኛችሁት ሌላ ነገር አለ?
የቤተሰብ አምልኳችሁን ማሻሻላችሁን ቀጥሉ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
-
ልጆች ከሌሉ አንድ ባል የቤተሰብ አምልኮውን ለሚስቱ አስደሳች ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 13 አን. 17-24