የይሖዋ ወዳጅ ሁን
እንደ ሙሴ የዋህ መሆን እፈልጋለሁ
በመሽሎክሎኪያው አልፎ መድረሻው ጋ እንዲደርስ ሙሴን አግዙት፤ እግረ መንገዳችሁንም ስለ ሙሴ ባሕርይ ተማሩ።
ወላጆች፣ ዘኁልቁ 12:3ን ከልጆቻችሁ ጋር ካነበባችሁ በኋላ ተወያዩበት።
ይህን መልመጃ አውርዳችሁ አትሙት።
ሙሴ፣ እስራኤላውያንን እንዲመራ ይሖዋ የመረጠው ሰው ነው። ሙሴ፣ የዋህ ሰው ተብሏል፤ ትልቅ ሥልጣን ቢኖረውም ሰዎችን በደግነት የሚይዝ፣ ለስላሳ ባሕርይ ያለው ሰው ስለሆነ ነው እንዲህ የተባለለት። በመሽሎክሎኪያው አልፎ መድረሻው ጋ እንዲደርስ ሙሴን አግዙት፤ ከዚያም እንደ ሙሴ የዋህ መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።