ከታሪክ ማኅደራችን
በይሖዋ ምሥክሮች የቅርብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ቦታ ስላላቸው ክንውኖችና ሰዎች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
አጠቃላይ ታሪካዊ ዳሰሳ
ታሪካችን—ትላልቅ ስብሰባዎች
የይሖዋ ምሥክሮች የሚያካሂዷቸውን ትላልቅ ስብሰባዎች ታሪክ እናስቃኝህ።
ታሪካችን—ቲኦክራሲያዊ የግንባታ ሥራ
የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎችን እየገነቡ ያሉት ለምን እንደሆነ ተመልከት።
ታሪካችን—በፊልምና በቪዲዮ ማስተማር
የይሖዋ ምሥክሮች ከ100 ለሚበልጡ ዓመታት በፊልምና በቪዲዮ አዘጋጅነት ያሳለፉትን ታሪክ እናስቃኝህ።
ምሥራቹን ለብዙኃን ማሰራጨት
የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክን መንግሥት መልእክት ለማሰራጨት የWBBR ሬዲዮ ጣቢያን የተጠቀሙት እንዴት ነው?
“እጅግ ክቡር ወቅት”
የጽዮን መጠበቂያ ግንብ የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል የሚከበርበትን ወቅት ‘እጅግ ክቡር ወቅት በማለት የጠራው ሲሆን አንባቢዎቹ በዓሉን እንዲያከብሩ አበረታቷል።በቀድሞዎቹ ዘመናት የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው እንዴት ነበር?
ታሪካችን—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 1
የሙዚቃ ታሪካችንን እናስቃኝህ፤ መዝሙርን ጨምሮ ሙዚቃ በይሖዋ ምሥክሮች የአምልኮ ሥርዓት ውስጥ የነበረውን የጎላ ድርሻ ተመልከት።
ታሪካችን—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 2
ባለፈው መቶ ዓመት የይሖዋ ምሥክሮች ለአምልኮ ይጠቀሙባቸው የነበሩ የተለያዩ የመዝሙር መጽሐፎችን ተመልከት።
‘ገና መሠራት ያለበት ብዙ የመከር ሥራ አለ’
በብራዚል የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚያሠራጩ ከ760,000 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች አሉ። የስብከቱ ሥራ በደቡብ አሜሪካ የተጀመረው እንዴት ነው?
ካፊቴሪያውን የሚያንቀሳቅሰው ፍቅር እንደሆነ ተመልክቷል
የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ትላልቅ ስብሰባዎች ላይ መገኘት የጀመርከው በ1990ዎቹ ዓመታት ወይም ከዚያ ወዲህ ከሆነ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ስለነበረ አንድ ዝግጅት ስትሰማ ትገረም ይሆናል።
ፖርቱጋል ውስጥ የመንግሥቱ ዘሮች የተዘሩበት መንገድ
በፖርቱጋል የነበሩት የመጀመሪያዎቹ የመንግሥቱ ሰባኪዎች የትኞቹን እንቅፋቶች ተወጥተዋል?
ከ1870 እስከ 1918
የሕዝብ ንግግሮች አየርላንድ ውስጥ ምሥራቹን አስፋፉ
ቻርልስ ቴዝ ራስል በአየርላንድ “ለመሰብሰብ የደረሰ አዝመራ” እንዳለ የተሰማው ለምንድን ነው?
አንድ መቶ ዓመት ያስቆጠረ የእምነት ገድል
በዚህ ዓመት፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ስለመሆኑ ጠንካራ እምነት እንዲኖራቸው ለመርዳት ሲባል የተዘጋጀው “የፍጥረት ፎቶ ድራማ” ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ ከበቃ 100 ዓመት ይሞላዋል።
“ዩሬካ ድራማ” ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዲያገኙ ረድቷል
አጠር ባለ መንገድ የተዘጋጀው “ዩሬካ ድራማ” ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ሌላው ቀርቶ ኤሌክትሪክ በሌለባቸው ቦታዎች እንኳ ሊታይ የሚችል ነበር።
‘ለይሖዋ ውዳሴ ማቅረብ’
የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ስለ ገለልተኝነት የተሟላ እውቀት ባይኖራቸውም በቅንነት ያከናወኑት ሥራ ጥሩ ውጤት አስገኝቷል።
‘በፈተና ሰዓት’ በአቋማቸው ጸንተዋል
አንደኛው የዓለም ጦርነት በ1914 ሲፈነዳ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የሚከተሉት የገለልተኝነት አቋም በይፋ የታወቀው እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
ከ1919 እስከ 1930
“ሥራው በኃላፊነት ለተሰጣቸው ሁሉ”
በ1919 ከተካሄደ ትልቅ ስብሰባ በኋላ በዓለም ዙሪያ ለውጥ ያመጣ ሥራ ተጀመረ።
“ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ልባችን በቅንዓትና በፍቅር ተሞልቶ ነበር”
የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቹ በ1922 ካደረጉት ትልቅ ስብሰባ በኋላ ‘ንጉሡንና መንግሥቱን አስታውቁ’ የሚለውን ምክር ተግባራዊ ያደረጉት እንዴት ነው?
‘እስከ ዛሬ ተሰምቶ የማያውቅ ግሩም መልእክት’
በ1926 የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች (በወቅቱ የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠሩበት ስም ነው) በአራት የካናዳ ከተሞች ውስጥ የራሳቸው የሬዲዮ ጣቢያዎች ነበሯቸው።
በፀሐይ መውጫዋ ምድር ጎሕ ቀደደ
“ኢዩዎች” የተባሉ ልዩ ተሽከርካሪዎች በጃፓን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለማስፋፋት አገልግለዋል።
ወቅታዊ የሆነ “ፈጽሞ የማይረሳ” ፊልም
አዲሱ የፍጥረት ድራማ፣ በጀርመን የነበሩ የይሖዋ ምሥክሮች በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወቅት የደረሰባቸውን የእምነት ፈተና እንዲቋቋሙ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
“ይሖዋ ወደ ፈረንሳይ ያመጣችሁ እውነትን እንድትማሩ ነው”
ፈረንሳይና ፖላንድ በ1919 የተፈራረሙት ስምምነት ያልተጠበቁ ውጤቶችን አስገኝቷል።
“ቤቴ ምንጊዜም ከእኔ ጋር ነበር”
በ1929 መገባደጃ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ የኢኮኖሚ ድቀት ተከስቶ ነበር። ታዲያ የሙሉ ጊዜ ሰባኪዎች እንዲህ ያለውን የኢኮኖሚ ቀውስ ተቋቁመው መኖር የቻሉት እንዴት ነው?
ከ1931 እስከ ዛሬ
የበላይ አካሉ አንድነትን ያጠናክራል—ክፍል 1
የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል፣ በዓለም ዙሪያ ካሉ ወንድሞችና እህቶች ጋር ያለውን ቅርበት ጠብቆ መቀጠል የቻለው እንዴት ነው?
የበላይ አካሉ አንድነትን ያጠናክራል—ክፍል 2
የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል፣ በዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበር ውስጥ አንድነት ለማስፈን ምን አድርጓል?
በከባድ ጊዜ በመንፈሳዊ ጠንካራ ሆነው ቀጥለዋል
በአውሮፓ ባሉ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የታመሱ አካባቢዎች የሚኖሩ ወንድሞች ሕይወታቸው ከባድ ነበር። ያን ፈታኝ ጊዜ ካሳለፉት ከእነዚህ ወንድሞች ተሞክሮ ምን ትምህርት እናገኛለን?
በተከፋፈለ አገር ውስጥ በአንድነት መኖር
በደቡብ አፍሪካ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች የአፓርታይድ ሥርዓትን ያሳለፉት እንዴት ነበር? ደግሞስ እነሱ ያሳለፉት ታሪክ ለእኛ ምን ትምህርት ይዞልናል?
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚያስተምር የባሕል ድርጅት
በሜክሲኮ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ለ50 ዓመታት በሕግ የተመዘገቡት እንደ ሲቪልና ባሕል ማኅበር ነበር። በአምልኳችን ላይ ገደብ ቢጣልም ይሖዋ ሥራችንን ባርኮታል።
“ከፀሐይ በታች ምንም ነገር ሊያግዳችሁ አይገባም!”
በ1930ዎቹ በፈረንሳይ የነበሩ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የቅንዓትና የጽናት ምሳሌ ናቸው።
“በጣም አስቸጋሪ ወይም በጣም ረጅም የሆነ መንገድ የለም”
በ1920ዎቹ መገባደጃና በ1930ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የነበሩ ቀናተኛ አቅኚዎች የአምላክን መንግሥት ምሥራች በአውስትራሊያ ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ለማዳረስ በትጋት ሠርተዋል።
“ቀጣዩን ትልቅ ስብሰባ የምናደርገው መቼ ይሆን?”
በ1932 የተደረገ 150 ሰዎች ብቻ የተገኙበት የአውራጃ ስብሰባ ይህን ያህል ትኩረት የሳበው ለምንድን ነው?
ንጉሡ እጅግ ተደሰቱ!
የስዋዚላንድ ንጉሥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን በአድናቆት የተቀበሉት እንዴት እንደሆነ አንብብ።
በደቡብ ምሥራቅ እስያ የእውነት ብርሃን ፋና ወጊ የሆነችው ላይትቤረር
ላይትቤረር በተባለችው ጀልባ ይጓዙ የነበሩት ጥቂት ወንድሞች ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም ብዙ ሕዝብ በሚኖርበት ሰፊ የሆነ ክልል የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በድፍረት አውጀዋል።
ሚሊዮኖች የሚያውቁት ባለ ድምፅ ማጉያ መኪና
ከ1936 እስከ 1941 ባለው ጊዜ ውስጥ “የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የድምፅ መኪና” በብራዚል የሚገኙት ጥቂት አስፋፊዎች የመንግሥቱን መልእክት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ማዳረስ እንዲችሉ ረድቷቸዋል።
“በብሪታንያ የምትገኙ የመንግሥቱ አስፋፊዎች—ንቁ!”
በብሪታንያ ውስጥ ለአሥር ዓመታት ያህል በመንግሥቱ አስፋፊዎች ቁጥር ላይ ያን ያህል ጎልቶ የሚታይ እድገት አልነበረም! በመጨረሻ ይህ ሁኔታ ሊቀየር የቻለው እንዴት ነው?
የኒው ዚላንድ የይሖዋ ምሥክሮች—ሰላማዊ እና ታማኝ ክርስቲያኖች
የይሖዋ ምሥክሮች በ1940ዎቹ ለማኅበረሰቡ ደኅንነት አደገኛ እንደሆኑ ተደርገው የተቆጠሩት ለምንድን ነው?
ምርጣቸውን ሰጥተዋል
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንዳበቃ የይሖዋ ምሥክሮች በጀርመን ያሉ የእምነት ባልንጀሮቻቸውን የረዱት እንዴት ነው?
ዓለም አቀፍ የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ
የተለያዩ አገሮች ባለሥልጣናት፣ የይሖዋ ምሥክሮች መሠረተ ትምህርትን ለማስፋፋት ጥረት በማድረጋቸው አመስግነዋቸዋል።
ኑሮ ከባድ ቢሆንም ይሖዋን ማገልገል
በፊሊፒንስ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች በ1970ዎቹና በ1980ዎቹ ዓመታት ከባድ የኢኮኖሚ ችግሮችን በጽናት ተወጥተዋል። ከፊታችን ከባድ ጊዜ የሚጠብቀን እኛ ከእነሱ ምሳሌ ምን እንደምንማር ተመልከት።
ታሪካችን—ሜፕስ ‘በሁሉም ቋንቋ’ ለመስበክ ይረዳናል
የይሖዋ ምሥክሮች በወረቀትም ሆነ በኤሌክትሮኒክ ፎርማት ጽሑፎች የሚያዘጋጁባቸው ቋንቋዎች ብዛት ከ1,000 ይበልጣል፤ ለዚህ ሥራ እንዲያግዛቸው ምን ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙ ተመልከት።