‘በማየት ሳይሆን በእምነት ተመላለሱ’
ኢየሩሳሌምን ከብቦ የነበረው የሮም ሠራዊት ባልታወቀ ምክንያት አፈገፈገ። ክርስቲያን የሆኑ ሁለት ቤተሰቦች ከፊታቸው ከባድ ውሳኔ ተደቅኗል። ኢየሱስን በመታዘዝ ሁሉን ነገር ትተው ከአገራቸው ይወጡ ይሆን? የሚያደርጉት ውሳኔ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ነው። ይህ ቪዲዮ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገቡና ከታሪክ አኳያ ትክክለኛ የሆኑ ክስተቶችን ያሳያል። የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ያጋጠማቸውን እውነተኛ ሁኔታ ለማሳየት ሲባል በፊልሙ ላይ ያልተጋነኑ የዓመፅ ድርጊቶች ይታያሉ።