በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቆም ላንድ አፍታ

ቆም ላንድ አፍታ

አውርድ፦

  1. 1. እሳት አንድደን ማታ፣ ሰብሰብ ብለን ጠጋ፤

    በከዋክብት ፈርጥ፣ ምሽቱ ሲያጌጥ፣ ልብ ለልብ እናውጋ።

    የሱን ጥሩነት ያንሳ፣ ሁሉም በየተራው፤

    ውሏችን የ’ለቱን፣ ተወት አ’ርገን ላሁን፣ ይመስጠን ሥራው።

    (አዝማች)

    እስቲ ትንሽ ጥሞና፣ እሱን ማሰቢያ፤

    ዝግ ይበል፤ ሩጫችን ይገታ።

    የመኖርን ጣ’ም፣ ለማጣጣም በ’ርጋታ፤

    ግድ ይላል ፋታ፤

    ቆም ላንድ አፍታ!

  2. 2. የሌቱ ሰማይ ጌጥ ሞገስ፣ ደምቃለች ጨረቃ፤

    ታ’ምር ነው ተፈጥሮ፣ ላየው አስተውሎ፣ መንፈስ የሚያነቃቃ።

    እናስታውስ ያ’ረገልንን፤ መች ያልቃል ተቆጥሮ?

    በኑሮ ብክንክን፣ ያደርገናል ስክን፣ ፍቅሩን ማሰብ ቆም ብሎ።

    (አዝማች)

    እስቲ ትንሽ ጥሞና፣ እሱን ማሰቢያ፤

    ዝግ ይበል፤ ሩጫችን ይገታ።

    የመኖርን ጣ’ም፣ ለማጣጣም በ’ርጋታ፤

    ግድ ይላል ፋታ፤

    ቆም ላንድ አፍታ!

    ቆም ላንድ አፍታ!

    ቆም ላንድ አፍታ!

    (አዝማች)

    እስቲ ትንሽ ጥሞና፣ እሱን ማሰቢያ፤

    ዝግ ይበል፤ ሩጫችን ይገታ።

    የመኖርን ጣ’ም፣ ለማጣጣም በ’ርጋታ፤

    ግድ ይላል ፋታ፤

    ቆም ላንድ አፍታ!

    (መደምደሚያ)

    ጊዜ ማሰቢያ፣ ለጥሞና፣

    ግድ ይላል ፋታ፤

    ጊዜ ማሰቢያ፣ ለጥሞና፣

    ሰከን፣ ትንሽ ፋታ፤

    ቆም ላንድ አፍታ!