ኦሪጅናል መዝሙሮች

ለመንፈሳዊ ውርሻችን ያለንን አድናቆት የሚገልጹ መዝሙሮች።

ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል (የ2025 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

ኢየሱስ በደስታ እንደታዘዘ ሁሉ እኛም የአምላክን ፈቃድ ማድረጋችን ደስታ ያስገኝልናል።

ደርሷል በቃ

አዲሱ ዓለም ገብተን በረከቶቹን የምናጣጥምበት ጊዜ በጣም ደርሷል።

በእጅህ ነኝ

ይሖዋ ማንነትህን እንዲቀርጸው ስትፈቅድ ሕይወትህ ይቀየራል።

የሰላም ሰው

ሰላማዊ ሰው ስንሆን ይሖዋ ይከበራል።

ለይሖዋ ክብር ስጡ

ለይሖዋ ያለን ፍቅርና አድናቆት ለእሱ ክብር እንድንሰጥ ያነሳሳናል።

በብርታትህ ልበርታ

ይሖዋ “ብቸኛ ለሆኑ ሰዎች መኖሪያ ቤት” የሚሰጣቸው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ይቅርብን ጓዙ

ይሖዋ በሚሰጠን መሠረታዊ ነገሮች ረክተን ከኖርን ደስተኞች እንሆናለን።

ቆም ላንድ አፍታ

ይሖዋ የፈጠራቸውን ነገሮች ማሰብ ሰከን ለማለትና የኑሮን ውጣ ውረድ ለማሸነፍ የሚረዳን እንዴት ነው?

‘እውነተኛው ሕይወት’

በተስፋችን ላይ ማሰላሰል ዛሬ የሚያጋጥመንን መከራ በጽናት ለማለፍ ብርታት ይሰጠናል።

ወንጌል (የ2024 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

ከመጀመሪያው መቶ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌል ሲታወጅ ኖሯል፤ ይህ ተልዕኮ፣ በትውልዶች ሁሉ ግለሰቦች በደስታ የተካፈሉበት፣ ብዙ ዋጋ የከፈሉለት እንዲሁም ኢየሱስ ራሱ የሚመራውና በመላእክት የሚደገፍ ክቡር ሥራ ነው።

‘ሰላሜ እንደ ወንዝ’

ይሖዋ የሚሰጠው ሰላም እንደ ወንዝ ነው፤ ለዘላለም ሳይቋረጥ ይፈስሳል።

እተጋለሁ ለእምነቴ

ጥርጣሬ ቤት ሳይሠራ ለእምነትህ ትጋ።

በእቅፉ

ወደ ይሖዋ ቤት ለመመለስ አሁንም አልረፈደም።

ዝም አንልም

በይሖዋ ታመን፤ ፍርሃትህን አሸንፈህ መስበክህን ቀጥል።

ያውቃል

ይሖዋ እያንዳንዳችንን በግለሰብ ደረጃ ያውቀናል፤ የውስጥ ስሜታችንን ይረዳል።

ሁለት ሳንቲም

የቱንም ያህል ትንሽ ቢመስል፣ ይሖዋ መሥዋዕትህን ያደንቃል።

ሰላም ሲያዜም ፍጥረት

ይሖዋን ማገልገላችን ሰላም ሰጥቶናል።

አቀረበኝ

ያሳለፉት ሕይወት ምንም ይሁን ምን፣ አምላክ ወዳጆቹ መሆን የሚፈልጉ ሰዎችን ሊያቀርባቸው ፈቃደኛ ነው።

‘አይዘገይ ከቶ!’ (የ2023 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

ይሖዋን በትዕግሥት ስትጠባበቅ ታማኝ አገልጋዮቹ የተዉትን ምሳሌ ተከተል።

አልኖርክም ገና!

ዛሬም ሆነ ወደፊት አስደሳችና ትርጉም ያለው ሕይወት አጣጥም!

ድክመትህ ላይ ንገሥ

ከስህተትህ ተማር እንጂ ተስፋ አትቁረጥ፤ የትናንቱን ትተህ ለነገው ማንነትህ ሥራ።

እንታረቅ

በደልን መተውና መታረቅ አይሻልም?

ይሖዋን ይዤ

በይሖዋ እርዳታ ፍርሃታችንን ማሸነፍ እንችላለን።

ወደ ማን እሄዳለሁ?

የአንድን ታማኝ የይሖዋ አገልጋይ የሕይወት ዘመን እንቃኝ። ዕድሜውን ሁሉ የእረኛውን ድምፅ የሰማው እንዴት ነው?

የናፈቀን ሰላም! (የ2022 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

ዛሬ ሕይወት በመከራ የተሞላ ቢሆንም እውነተኛ ሰላም እንደሚሰፍን አምላክ የገባው ቃል ያጽናናናል።

አንድ ላይ እንጽና

በወንድማማች ማኅበራችን እና በይሖዋ እርዳታ ማንኛውንም ፈተና በጽናት መቋቋም እንችላለን።

የይሖዋ ቤተሰብ

በዓለም ላይ እውነትን እየፈለጉ ያሉ ሰዎች አሁንም አሉ። ይህ ቪዲዮ፣ እንዲህ ዓይነቶቹን ቅኖች መፈለግህን እንድትቀጥል ያነሳሳሃል።

ጊዜ ስጠው ለሱ

ይሖዋን በትጋት ማገልገል ከሁሉ የተሻለ የሕይወት መንገድ ነው።

እይማ

አዲስ ዓለም እንደሚመጣ በሚገልጸው ተስፋ ደስ ይበልህ።

ጉልበትህን ስጠው ላምላክህ

ጉልበትህን ይሖዋን ለማገልገል ተጠቀምበት። መቼም አይቆጭህም!

‘ደስ ይበለን’

ለመደሰት የሚያበቁንን ብዙ ምክንያቶች የሚያስታውስ መዝሙር።

በእምነት ዓይኔ

አምላክ ወደፊት ለሰው ልጆች የሚሰጣቸው ሕይወት ምን ያህል አስደናቂ እንደሆነ በዓይነ ሕሊናህ ለመሣል ሞክር።

አንድ ሕዝብ ሆነናል

ብዙ ችግርና ፈተና ቢያጋጥመንም ምንጊዜም አንድ ሕዝብ ነን።

ልቤን እጠብቃለሁ

በይሖዋ እርዳታ፣ ልብህ በሚያስጨንቁ ሐሳቦች እንዳይወጠር በምታደርገው ትግል አሸናፊ መሆን ትችላለህ።

ውዴ፣ የኔ

የይሖዋ ስጦታ በሆነው በትዳር ተደሰት።

እንጸናለን

ጠንካራ እምነት ለመገንባት ጥራት ያለው ጥሬ ዕቃ ያስፈልጋል።

እንሩጥ

በሕይወት ሩጫ አሸናፊ ለመሆን ጥሩ ውሳኔዎችን አድርግ።

በነፃ ይቅር እንድል

ስሜትህን የጎዳው ሰው አለ? በደሉን መርሳት ከብዶሃል? በነፃ ይቅር ማለት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የዘላለም ደስታ

ይሖዋ አሁንም ሆነ ለዘላለም ደስታችን ነው።

እርግጠኛ ሁን

ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን ይሖዋ እንደሚወደን እርግጠኛ መሆን እንችላለን።

እንደ ልጆች

ፍቅር በማሳየት ረገድ እንደ ልጆች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

ተወው ለሱ

በጭንቀት ስትዋጥ ይሖዋን እንዲረዳህ ለምነው፤ ያጠነክርሃል እንዲሁም ያጽናናሃል።

ያንተው ትሁን ነፍሴ

ለይሖዋ ያለን ፍቅር ራሳችንን ለእሱ እንድንወስንና እንድንጠመቅ ያነሳሳናል።

ፍቅር ለዘላለም ይኖራል

የይሖዋ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል። ደስታና መጽናኛ ይሰጠናል።

ያ አዲስ ዘመን

በዓይነ ሕሊናችን የምንስለው ነገር በአስተሳሰባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህ መዝሙር ስለ አዲሱ ዓለም እንድናስብ ይረዳናል።

ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም

ይሖዋ ምንጊዜም ሊረዳን ፈቃደኛ ነው።

“መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል”

ከችግሮቻችን ጋር መታገል ቢኖርብንም ለይሖዋ ታማኝ መሆን እንችላለን።

አንድ ቤተሰብ

የትም ብንሆን አንድ ቤተሰብ ነን።

ደፋር እና ብርቱ

እንድንጸና የሚያበረታታን ተወዳጅ መዝሙር።

ድፍረት ስጠኝ

ይሖዋ የትኛውንም ፈተና መቋቋም እንድንችል ድፍረት ይሰጠናል።

አይተወኝም ለብቻዬ

ይሖዋ አምላካችን መቼም ብቻችንን አይተወንም!

ተዋደን እንኑር

ይሖዋ በትዳራችሁ ውስጥ እንዲኖር ከፈቀዳችሁ ጥምረታችሁ ጠንካራ ይሆናል!

እዚያው አልቀርም

ቀደም ሲል ቀናተኛ የይሖዋ አገልጋይ የነበረች ሴት ወደ ጉባኤው ለመመለስ የሚያስችል ኃይል ያገኘችው እንዴት ነው?

ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ

የይሖዋን ማሳሰቢያዎች እንደምንወድ በንግግራችንም ሆነ በተግባራችን እናሳይ።

በእምነት ይሳካል

ጠንካራ እምነት መገንባት ጥረት ይጠይቃል፤ ሆኖም ጥረት ካደረግን ይሖዋ ይባርከናል።

ውሳኔ

የግል ውሳኔዎቻችን አገልግሎታችንን እና ሌሎች ሰዎችን የሚነኩት እንዴት እንደሆነ ማሰባችን ጥበብ ነው።

ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ

ወደፊት ስለሚመጣው ገነት ማሰባችን እንድንጸና ይረዳናል።

እናመስግንህ

ይሖዋ ቅዱስ መንፈሱን በመስጠት፣ የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድንቋቋም ይረዳናል። ለዚህ ዝግጅት ያለን አድናቆት እሱን በመዝሙር እንድናወድሰው ያነሳሳናል።

ያ ቀን ይታይህ

በቅርቡ ሁሉ ነገር አዲስ ይሆናል።

ስብሰባ የሚያስገኘው ደስታ

በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝ በዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን ውስጥ ያለውን አንድነትና ፍቅር የመመልከት አጋጣሚ እናገኛለን።

ፈገግታ

በአገልግሎታችን ላይም ሆነ ኑሮ በሚወስደን ቦታ ሁሉ ፈገግታ ማሳየት ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

አሁኑኑ

የአቅኚነት መንፈስ ለሰዎች ፍቅር እንድናሳይ ይገፋፋናል።

ይቅርታ ከመረጥከው ጋር የሚዛመድ ቃል የለም።