በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 100

የይሖዋ ሠራዊት ነን!

የይሖዋ ሠራዊት ነን!

(ኢዩኤል 2:7)

1. ነን የአምላክ ሠራዊት፣

ነፃ የወጣን።

በ’የሱስ ’ሚመራውን

መንግሥት እንሰብካለን።

እንገፋለን ወደፊት፣

በታማኝነት።

አለን ጽኑ አቋም፤

ቅንጣት አንፈራም።

(አዝማች)

ነን የአምላክ ሠራዊት፣

ከ’የሱስ ጋር አንድ፤

መግዛት መጀመሩን

በደስታ ’ናውጅ።

2. ነን የአምላክ አገልጋይ፣

እንፈልጋለን

የባዘኑ በጎችን፤

’ሚያለቅሱ፣ ’ሚያዝኑትን።

እንርዳቸው ቅኖችን

ሳንሰለች ሄደን።

እንጋብዛቸው ሁሌ፣

ወደ ጉባኤ።

(አዝማች)

ነን የአምላክ ሠራዊት፣

ከ’የሱስ ጋር አንድ፤

መግዛት መጀመሩን

በደስታ ’ናውጅ

3. ይህ ያምላክ ሠራዊት ነው፤

’የሱስ ’ሚመራው።

የጦር ትጥቁን ያሟላ፤

’ማይል ወደኋላ።

ግን ቆመን በተጠንቀቅ

ሁሌም እንጠብቅ፤

በአስቸጋሪ ወቅት፣

እንጽና በ’ውነት።

(አዝማች)

ነን የአምላክ ሠራዊት፣

ከ’የሱስ ጋር አንድ፤

መግዛት መጀመሩን

በደስታ ’ናውጅ

(በተጨማሪም ኤፌ. 6:11, 14⁠ን፣ ፊልጵ. 1:7⁠ን እና ፊል. 2⁠ን ተመልከት።)