መዝሙር 97
እናንት የመንግሥቱ ሰባኪዎች ወደፊት ግፉ!
1. ግፉ ወደፊት አሰራጩ፤
ለሁሉም ሰው ወንጌሉን።
ልባችን በፍቅር ተገፍቶ፣
እንርዳ ቅን ሰዎችን።
ክብር ነው ማገልገል አምላክን፤
ለሌሎች መመሥከር ቃሉን።
እንውጣ ለስብከት ወደ መስክ፤
ያምላክን ስም እናሳውቅ።
(አዝማች)
ሂዱ፣ ግፉ፣
በሁሉም ቦታ ወንጌሉን አስፋፉ።
በርቱ፣ ግፉ፣
ለይሖዋ ቁሙ፣ እሱን ደግፉ።
2. ያምላክ አገልጋዮች ገስግሱ፤
አለላችሁ ሽልማት።
የጌታን ፈለግ እንከተል፤
ልባችንን በማንጻት።
ስለ መጪው የአምላክ መንግሥት፣
ሰው ሁሉ መስማት አለበት።
ንሰብካለን ባምላክ ብርታት፤
አንሸነፍም ለፍርሃት።
(አዝማች)
ሂዱ፣ ግፉ፣
በሁሉም ቦታ ወንጌሉን አስፋፉ።
በርቱ፣ ግፉ፣
ለይሖዋ ቁሙ፣ እሱን ደግፉ።
3. ሌሎች በጎችም ሆን ቀሪዎች፣
ፆታ ዕድሜ ሳንለይ፣
በእውነት መንገድ ላይ እንሂድ፤
ተያይዘን ባንድ ላይ።
ቅዱስ ነው አገልግሎታችን፤
አናመልክም በዘልማድ።
ቅዱስ ሥነ ምግባር ከኖረን፣
ዋጋ አለን በአምላክ ዘንድ።
(አዝማች)
ሂዱ፣ ግፉ፣
በሁሉም ቦታ ወንጌሉን አስፋፉ።
በርቱ፣ ግፉ፣
ለይሖዋ ቁሙ፣ እሱን ደግፉ።
(በተጨማሪም መዝ. 23:4ን፣ ሥራ 4:29, 31ን እና 1 ጴጥ. 2:21ን ተመልከት።)