በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 50

መለኮታዊው የፍቅር መንገድ

መለኮታዊው የፍቅር መንገድ

(1 ዮሐንስ 4:19)

1. ይሖዋ አምላክ በጥበቡ ሰጠ

ለሁሉም፣ ለሁሉም።

የፍቅርን መንገድ እንድንመራበት፤

እንዳንወድቅ፣ እንዳንወድቅ።

መንገዱን ሁሌ ’ንከተል ይጠቅማል፤

ለመልካም ሥራ ያንቀሳቅሰናል፤

ለአምላክ ሕዝቦች አንድነት ያስገኛል።

ነው ይህ መንገድ፤

የፍቅር መንገድ።

2. ለወንድማችን ያለን ፍቅር ይሁን

የእውነት፣ የእውነት።

ወንድሞቻችን ሲቸገሩ መርዳት

ደስ ይለናል፣ ደስ ይለናል።

ሌሎችን ይቅር ማለት ይቀለናል፤

መዋደዳችን የእውነት ይሆናል፤

ይህም አምላክን መምሰል ያስችለናል።

ይታይ ፍቅር፤

ልባዊ ፍቅር።

3. ያነሳሳናል ላምላክ ያለን ፍቅር

ለስብከት፣ ለስብከት።

እንታዘዘው ሁሌም ከልባችን፤

’ናወድሰው፣ ’ናወድሰው።

ስሙን እናስታውቅ ለሚሰሙ ሁሉ፤

እናብራላቸው እውነትን ከቃሉ።

ላገልግሎቱ ፍቅራችን ይጨምር፤

ይህ ነው ፍቅር፤

የእውነት ፍቅር።

(በተጨማሪም ሮም 12:10⁠ን፣ ኤፌ. 4:3⁠ን እና 2 ጴጥ. 1:7⁠ን ተመልከት።)