በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 70

የሚገባቸውን ሰዎች ፈልጉ

የሚገባቸውን ሰዎች ፈልጉ

(ማቴዎስ 10:11-15)

  1. 1. እንዴት መስበክ እንዳለብን ነግሮናል፤

    ጌታ መመሪያ ሰጥቶናል፦

    ‘በሁሉም ስፍራ ፈልጉ ቅኖችን፤

    በመንፈሳዊ ’ሚራቡትን።

    ለቤተሰቡ ሰላምን ተመኙ፤

    ’ሚገባው ከሆነ ይድረሰው።

    እምቢ ካሉ ግን የ’ግራቹን አቧራ

    አራግፋችሁ ሂዱ፣ ተዉአቸው።’

  2. 2. ’ሚቀበላችሁ ጌታን ይቀበላል።

    ልቡ ይከፈትለታል።

    ጥሩ የልብ ዝንባሌ ስላለው፣

    እሱም ማገልገል ይጀምራል።

    ‘ምን እንላለን?’ ብላችሁ አትስጉ፤

    ይረዳችኋል አምላካችሁ።

    ንግግራችሁ ቢሆን ለዛ ያለው፣

    ይሳባል ቅንና ትሑት ሰው።

(በተጨማሪም ሥራ 13:48⁠፤ 16:14⁠ን እና ቆላ. 4:6⁠ን ተመልከት።)