መዝሙር 50
ራሴን ለአምላክ ለመወሰን ያቀረብኩት ጸሎት
-
1. ጥበብን ይውደድ ልቤ፤
ያስደስትህ ሐሳቤ።
ላንተ ክብር፣ ውዳሴ
ልዘምር ባንደበቴ።
-
2. ከት’ዛዝህ አልወጣም፤
ሕጎችህን አልረሳም።
አልሳሳም ለንብረቴ፤
ያንተ ነው ውድ አባቴ።
-
3. ሕይወቴም የአንተው ነው፤
ፈቃድህን እሻለሁ።
ምንም ሳልቆጥብ ራሴን፣
እሰጥሃለሁ ነፍሴን።
(በተጨማሪም መዝ. 40:8ን፣ ዮሐ. 8:29ን እና 2 ቆሮ. 10:5ን ተመልከት።)