የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በjw.org ላይ ጥሩ የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ኩኪዎችንና ሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። አንዳንድ ኩኪዎች ድረ ገጹ እንዲሠራ የግድ ስለሚያስፈልጉ መከልከል አይቻልም። አጠቃቀምህን ለማሻሻል ብቻ የምንጠቀምባቸውን ሌሎች ተጨማሪ ኩኪዎች መፍቀድ ወይም መከልከል ትችላለህ። ይህ መረጃ በፍጹም አይሸጥም ወይም ለንግድ ዓላማ አይውልም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ገጽ ተመልከት፦ የኩኪዎችንና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ዓለም አቀፍ ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ ምርጫዎችን ማስተካከል ከፈለግክ ይህን ገጽ ተጠቀም፦ የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 36

ልባችንን እንጠብቅ

ልባችንን እንጠብቅ

(ምሳሌ 4:23)

  1. 1. ልባችንን እንጠብቅ፤

    ከኃጢያት እንራቅ፤

    አምላክ የተሰወረውን፣

    ያያል ልባችንን።

    አንዳንዴ ልብ ያታልላል፤

    ሊያስተን ይችላል።

    ለልባችን እንጠንቀቅ፤

    ከመንገድ እንዳንርቅ።

  2. 2. እናዘጋጅ ልባችንን

    ለማወቅ አምላክን።

    ጸሎት፣ ምስጋና፣ ውዳሴ

    እናቅርብ ሁልጊዜ፤

    ይሖዋ የሚነግረንን፣

    መታዘዝ አለብን።

    አምላክን ’ናስደስታለን፤

    ታማኝ ልብ ቢኖረን።

  3. 3. እንመግበው ልባችንን

    እውነት የሆነውን።

    ቃሉ ይንካን፣ ይለውጠን፤

    ያበርታን፣ ኃይል ይስጠን።

    አምላክ ይወዳል ሕዝቦቹን፤

    ይህን እናምናለን።

    በሙሉ ልብ እናምልከው፤

    ወዳጅ እናድርገው።

(በተጨማሪም መዝ. 34:1⁠ን፣ ፊልጵ. 4:8⁠ን እና 1 ጴጥ. 3:4⁠ን ተመልከት።)

 

ልባችንን እንጠብቅ