መዝሙር 34
በንጹሕ አቋም መመላለስ
(መዝሙር 26)
-
1. አምላኬ ሆይ፣ ’ባክህ ፍረድልኝ፤
ባንተ ታምኛለሁ፤ ንጹሕ አቋም አለኝ።
ልቤን ከፍተህ ውስጤን ተመልከተኝ፤
መጥፎ ነገር ቢገኝ እባክህ አጥራልኝ።
(አዝማች)
በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤
በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።
-
2. ካታላይ ጋር አልቀራረብም፤
ካስመሳዮችም ጋር አልተባበርም።
ካመፀኞች ጋር አታጥፋ ነፍሴን፤
ከግፈኞችም ጋር አታድርግ ዕጣዬን።
(አዝማች)
በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤
በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።
-
3. ወድጃለሁ ያምልኮ ቤትህን፤
የሙጥኝ ብያለሁ ንጹሕ አምልኮህን።
መሠዊያህን በደስታ ’ዞራለሁ፤
ምስጋናህን ሁሌ ለሰው አሰማለሁ።
(አዝማች)
በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤
በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።
(በተጨማሪም መዝ. 25:2ን ተመልከት።)