በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 144

ዓይንህ ሽልማቱ ላይ ያተኩር!

ዓይንህ ሽልማቱ ላይ ያተኩር!

(2 ቆሮንቶስ 4:18)

  1. 1. ማየት፣ መስማት የተሳናቸው

    ሲፈወሱ ይታይህ ደስታው!

    የሕፃናት ሳቅ ሲያስተጋባ፣

    የትም ሲያብብ ሰላም ደስታ፣

    ሙታን ሲወጡ ከመቃብር፣

    ኃጢያት፣ ዓመፅ ጠፍቶ ከምድር፣

    (አዝማች)

    ተስፋው ላይ ካተኮረ ዓይንህ፣

    በዚህ ጊዜ ትኖራለህ።

  2. 2. ተኩላ ከጠቦት ጋር ይውላል፤

    ጥጃ ከድብ ጋር ይሰማራል።

    ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል፤

    እነሱም ይታዘዙታል።

    ታሪክ ሲሆን እንባና ለቅሶ፣

    ሥቃይ፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት ተረስቶ፣

    (አዝማች)

    ተስፋው ላይ ካተኮረ ዓይንህ፣

    በዚህ ጊዜ ትኖራለህ።

(በተጨማሪም ኢሳ. 11:6-9⁠፤ 35:5-7⁠ን እና ዮሐ. 11:24⁠ን ተመልከት።)